ጀርመን የ12.1 ሚሊዮን ዩሮ ተጨማሪ ድጋፍ አደረገች

Date:

የጀርመን ኤምባሲ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በተደረጉ አዳዲስ የትብብር ስምምነቶች መሠረት በ2026 የሚከናወኑ አራት አህጉራዊ ፕሮግራሞችን ለማጠናከር የ12.1 ሚሊዮን ዩሮ ተጨማሪ ድጋፍ ማድረጓን አስታወቀ።
 
ይህ ድጋፍ የአፍሪካ ህብረትን የ2063 አጀንዳ ለማገዝ፣ ቀጠናዊ ትስስርን ለማፋጠን፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥ እና የሕዝብ ጤናን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ድጋፉ በጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር (GIZ) በኩል የሚፈጸም ሲሆን፣ አራቱንም የትኩረት አቅጣጫዎች ያካተተ መሆኑን ጠቅሷል።
 
በኢትዮጲያ የጀርመን ኤምባሲ ለጣቢያችን በላከው መግለጫው መሠረት፣ ለመሰረተ ልማት እና ኢኮኖሚ ትስስር የተመደበው 5.6 ሚሊዮን ዩሮ የ”Africa InCORE” ፕሮግራምን ለማስፋፋት፣ አህጉራዊ ንግድን ለማፋጠን እና አረንጓዴ የኢኮኖሚ እድገትን የሚያበራቱ ትልልቅ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ይውላል።
 
በሌላ በኩል የልማት ፋይናንስ እና የታክስ ስርዓትን ለማጠናከር 3 ሚሊዮን ዩሮ የተመደበ መሆኑን የገለጸው ኤባሲው  ፣ ይህም ሕገ-ወጥ የፋይናንስ ፍሰትን ለመግታት፣ የብድር አስተዳደርን ለማሻሻል እና ከአፍሪካ የታክስ አስተዳደር ፎረም (ATAF) ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
 
በተጨማሪም የታደሱ የኃይል ምንጮችን እና የኃይል ማሰራጫ ስርዓቶችን በአህጉርና ቀጠናዊ ደረጃ ለማጠናከር በ”ENGAGE” ፕሮግራም በኩል 1.5 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚውል ኤምባሲው ገልጿል።
 
ለሕዝብ ጤና ዘርፍ የተመደበው 2 ሚሊዮን ዩሮ የአፍሪካ በሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከል ማዕከልን (Africa CDC) ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር፣ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመግታት እና የወደፊት የጤና ስጋቶች ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚውል ይሆናል ተብሏል።
 
ይህ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ጀርመን ከአፍሪካ ህብረት ጋር ያላትን ዘላቂ የልማት አጋርነት እና የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካውያን ተቋማት የመፍትሔ አቅም የመደገፍ ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል።
 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...