ገዳዩ ተይዟል !

Date:

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ

ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው

ብዙዎችን ያስቆጣው እና ያሳዘነው የዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ግድያ ወንጀል ፈጽሟል የተባለ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

በዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊቲ ሐኪም፣ ተመራማሪ፣ መምህር እና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር አንዱዓለም ዳኘ ባልታወቁ ኃይሎች መገደላቸው ይታወሳል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፖሊስ ባደረገው ክትትል እሱባለው ነበረ የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ብለዋል።

ወንጀል ፈጻሚው ድርጊቱን መፈጸሙን ማመኑንም ተናግረዋል። ግድያው ጥቅም ፍለጋ መኾኑን ተናግረዋል።

በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ተመሳሳይ ወንጀሎችን ይፈጽም እንደነበርም አንስተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...