ጉማ አዋርድ ከአሪፍ ፔይ ጋር በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ አካሄዷል። በፊርማ ስነስርአቱ ላይ እንደተገለጸው የዛሬው የፊርማ ስምምነት ጉማ አዋርድ የፊታችን ጥቅምት 2018 ላይ ለሚካሄደው የጉማ አዋርድ የአጋርነት ስራ ለመስራት እንደሆነ ተነግሯል
በዚህም አሪፍ ፔይ 11ኛውን የጉማ አዋርድ አጋር አዘጋጅ በመሆን አብሮ ይሰራል ተብሏል። እንዲሁም ጉማን በታይትል ስፓንሰርነት ለማገዝ እንደሆነም ተገልጿል
ጉማ ላለፉት 10 አመታት በተከታታይ ለህዝብ መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን በዚህ ረጅም አመታት ውስጥ ከ250 በላይ ዋንጫ የታደለ ወደ 800 እጩዎች የቀረቡ ከ200 በላይ ተሸላሚዎችን ይፋ አድርጓል፡፡
አሁን ደግሞ የሚቀጥለውን የ10 አመት ጉዞ ለመጀመር አንድ ተጨማሪ ፓርትነር (ARIFPAY) ጉማን በታይትል ስፓንሰርነት ከሚቀላቀለው አሪፍ ፔይ ጋር ተፈራርሟል።
