ግሎባል ባንክ ከ 1.17 ቢሊየን ብር በላይ አተረፈ

Date:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በብሔራዊ ባንክ የተጠየቀውን ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል በቀድሞ በማሟላት ወደ 5 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ገልፀዋል። ካለፈው ጋር ሲነፃፀርም 102% እድገት አሳይቷል።

ባንኩ በዚህ ዓመት 7.53 ቢሊዮን ብር አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ ሰብስቦ አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘቡን መጠን 25.75 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፣ ይህም 41% እድገት ኣይቷል።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከዓለም አቀፍ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ ጋር ተዳምሮ በሀገራችንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ሁኔታው አለመረጋጋት ያሳየ ቢሆንም ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ፣ ከመጠባበቂያ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ 1.17 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፍ ችሏል፡፡

በዲጂታል አገልግሎት ዘርፍ ባንኩ በሞባይል፣ በኢንተርኔት እና በUSSD አገልግሎት በመስጠት 636,000  ተጠቃሚዎችን አገልግሏል።

ባንኩ፥ ከካቻ ፋይናንሺያል ጋር በመተባበር የዲጂታል ቁጠባና ብድር አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን በኢንሹራንስ ዘርፍ የመጀመሪያው የኢንሹራንስ አረቦን ብድር አገልግሎት ጀምሯል።

በቅርንጫፍ ስፋትም ባንኩ በዚህ ዓመት 12 አዳዲስ ቅርንጫፎች በመከፈት አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ቁጥር 237 አድርሷል በፕሪሚየም ቅርንጫፎቹ በስታዲየም እና በሜክሲኮ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።

ባንኩ፥ በ2025 ዓ.ም በአፍሪካ ባንክና ኢንሹራንስ አዋርድ ላይ የአፍሪካ ምርጥ የቁጠባ ባንክ ሽልማት እና ከኢንተርናሽናል ስትራቴጂክ አሊያንስ ማዕከል የዲጂታል ፈጠራ እና ልህቀት ሽልማት አግኝቷል።

ባንኩ ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም 13ኛ መደበኛ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ያካሂዷል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ – “ለጋራ ስኬታችን”

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...