ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኩዌቱ አልጋ ወራሽ ጋር በስልክ ውይይት አደረጉ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኩዌቱ አልጋ ወራሽ ጋር በዛሬ ዕሁድ በስልክ ባደረጉት ውይይት፣ በኢራን የተፈጸመውን ጥቃት በጽኑ መኮነናቸውንና ኢትዮጵያ ከኩዌት ጎን መቆሟን መግለጻቸውን የኩዌት የዜና አገልግሎት (ኩና) ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ሳባህ ካሊድ አል-ሐማድ አል-ሳባህ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት፣ የኩዌትን ሉዓላዊነት፣ የአየር ክልል፣ ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርን የጣሰ ነው ያሉትን ጥቃት አውግዘዋል።

በውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ የኩዌትን የሲቪል ተቋማት ኢላማ ያደረገ ማንኛውንም ጥቃት እንደማትቀበል በግልጽ አስምረውበታል ተብሏል።

በተጨማሪም ኩዌት ሉዓላዊነቷን፣ መረጋጋቷን እና ደህንነቷን ለመጠበቅ ለምትወስደው ማንኛውም እርምጃ ኢትዮጵያ ለሀገሪቱ አመራሮች፣ መንግሥት እና ሕዝብ ያላትን ጽኑ ድጋፍ አረጋግጠዋል።

ይህ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተደረገው፣ ኢራን በባሕረ ሰላጤው ሀገራት ላይ የሰነዘረችውን የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት ተከትሎ ቀጣናዊ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው።

እንደ ኩና ዘገባ፣ አልጋ ወራሹ የኩዌቱ አሚር ሼክ መሻል አል-አሕመድ አል-ጃቢር አል-ሳባህ ለኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ሰላምታ በማስተላለፍ ኢትዮጵያ ለኩዌት ላሳየችው ጽኑ ድጋፍ ያላቸውን ጥልቅ አድናቆት ገልጸዋል። አልጋ ወራሹ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም “ልባዊ እና ወንድማማቻዊ” ላላቸው ቅድሚያ ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...