ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

Date:


👉 2017 ዓ.ም ይቻላል ተብለው ያልታሰቡ ጉዳዮች የተከናወኑበት እና የስኬት ዓመት ነበር፣

👉 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የግብርና መር ፖሊሲ ይከተል ነበር ይህንን ወደ ብዝሀ ዘርፍ ቀይረን በእጅጉ ውጤታማ ሆነናል፣

👉 በአንድ ሴክተር ላይ ተንተርሶ መስራት ከድህነት አረንቋ ስለማያወጣን ብዝሀ ዘርፍን በመከተላችን ውጤት አምጥተናል፣

👉 ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ እነዚህ አምስት ግንባር ቀደም ሴክተሮች ብዝሀ ዘርፍ ሆነው ቢመሩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሊያሻሽሉ ይችላ የሚል እምነት ነበረን፣

👉 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስር ነቀል ውጤት እንዲያመጣ ብዝሀ ዘርፍ መንግስት ከአጋር ድርጅቶች ጋር ተሳስሮ የኢትዮጵያ ዕድገት ለማፋጠን ይሰራል፣

👉 መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ የኢትዮጵያን ልማት በየፈርጁ ማፋጠን አለበት፤ በመንግስት ደረጃ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠለት ከለውጡ በኋላ ነው፣

👉 ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴ ባለፉት ዓመታት 48 ቢሊየን ችግኞችን ተክላለች፤ ይህም በዓለም ላይ ትልቁ የደን ልማት ነው።

👉 ይህንንም ለእያንዳንዱ ችግኝ 1 ዶላር ቢወጣ በጠቅላላው 48 ቢሊየን ዶላር ለአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያ ኢንቨስት አድርጋለች፣

👉 የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ያህል ገንዘብ ብቻውን ሊያሳካው አይችልም ነገር ግን ከ25 ሚሊየን በላይ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን በየአመቱ ጊዜያቸውን ጉልበታቸውን ሳይታክቱ በመስራታቸው ያንን ሚያክል ሃብት ያስወጣ የነበረን ስራ በመንግስት እና በህዝብ ቅንጅት ማሳካት ተችሏል።

👉 የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ መንግስት በቂ የፍጆታ ምርት አቅርቦት እንዲኖር እና የገበያ ትስስር እንዲጠናክር ማድረግ ችሏል፡፡

👉 የገበያ ትስስር በመፍጠር በተለይ በቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች፣ ነጋዴ እና ገዥን እንዲሁም ሻጭ እና አምራችን ማገናኘት ተችሏል፡፡

👉 በተጨማሪም የኑሮ ውድቱን ለማቃለል፤ በድጎማ ለሴፍቲኔት 60 ቢሊየን ብር ለማዳበሪያ 84 ቢሊየን ብር፣ ለነዳጅ 140 ቢሊየን ብር እንዲሁም ለደመወዝ 160 ቢሊየን ብር ድጎማ ተደርጓል፡፡

👉 በድምሩ 440 ቢሊየን ብር ለተለያዩ ድጎማዎች መንግስት ወጭ አድርጓል፡፡

👉 የተማሪዎች ምገባ፣ የማዕድ ማጋራት እንዲሁም የመንግስት የገንዘብ ፖሊሲ ለኑሮ ውድነቱ ለመከላከል በእጅጉ አግዟል፣

👉 የዚህ ወር የዋጋ ግሽበት 11 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ እንዲል ማድረግ ተችሏል።
👉 ኢትዮጵያ ትልቁ የምታወጣው ወጪ ለማዳበሪያ እና ነዳጅ ነው፤

👉 ዳንጎቴ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያለማው የማዳበሪያ ፋብሪካ 30 ሚሊየን ኩንታል ዩሪያ የሚያመርት ነው፣

👉 ቢሾፍቱ የሚሰራው አየር መንገድ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያመጣል፤ አየር መንገዱ ከ100 ሚሊየን በላይ ተጓዦችን በዓመት የሚያስተናግድ በመሆኑ ከአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ ይሆናል፣

👉 እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የቤት ባለቤት እንዲሆን ማድረግ የሚቻል አይደለም፤ ቢያንስ ሁሉም ሰው የኪራይ ቤት እንዳያጣ ማድረግ ያስፈልጋል፣

👉 የኮሪደር ልማት ዋና ዓላማው ያለንን ቦታ በአግባቡ እንድንጠቀም የሚያደርግ ነው፤ የኮሪደር ልማት የፈጠራ አቅም እና የኑሮ ዘዬን የቀየረ ነው፣

👉 አዲስ አበባ ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ ትንንሽ ስታዲየሞች ተገንብተዋል፤ የተገነቡት ትንንሽ ስታዲየሞች በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ተጫዋቾችን ያበረክታሉ።


👉 ኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ስፍራ የባሌን ያህል ሀብት የለውም፤ የባሌን ያህል ደግሞ ምንም ነገር ያልተሰራበት አካባቢ የለም፣

👉 የባሌ ህዝብ ጨዋ ህዝብ ነው ሃብቶቹን ጠብቆ እዚህ ማድረስ ችሏል፤ በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ በአግባቡ ጠብቆ በማቆየቱ መንግስት የባሌን ህዝብ ሊያመሰግን ይገባል፣

👉 ባሌ ውስጥ ከ2 ሺህ ሄክታር በላይ ብሔራዊ ፓርክ አለ፤ መብራት መንገድ የሌለው ቦታ ላይ ህዝቡ ይህንን ሃብት በጀግንነት ሃብቶቹን ጠብቆ በመኖሩ መንግስት ያመሰግናል፣

👉 ያንን የሚያክል ጫካ መጠበቅ ከባድ ነው፤ የባሌ ህዝብ አስደማሚ ህዝብ ነው፣

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ የባሌ ያክል ሃብት ያለው የለም የባሌን ያክል ስራ ያልተሰራበት ቦታም የለም፣

👉 የሶፍ ዑመር ዋሻን የተከበረው ምክር ቤት በአዋቂዎች በተመራማሪዎች እንዲታይ እንዲመረመር ሄዶ እንዲጠይቅ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፣

👉 የሶፍ ዑመር ዋሻ በጀግኖች የኢትዮጵያ ትውልዶች ተፈጥሮን መሰረት አድርጎ በከፍተኛ ድካም የተሰራ ስራ ነው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ያንን ቦታ ለማራከስ ካላቸው አቋም ውሃ የፈጠረው ዋሻ ብለው ትተውት ነበር፣

👉 ሶፍ ዑመር ከነበራቸው ህዝብ ጋር ውሃ ገድበውና የውሃ አቅጣጫ አስቀይረው የሰሩት ስራ ነው፣

👉 የሶፍ ዑመር ዋሻ በተጨማሪ በርካታ ዋሻዎች ባሌ ውስጥ ይታያል፤ የከረምነው ውሃ የፈጠረው ዋሻ የሚል ስንሰማ ነው፤ ግን ውሃ አዳራሽ አይፈጥርም ዋሻው መስገጃ ቦታም አለው።


👉 ፕሮጀክት በባህሪው እሳት ዳር እንደተቀመጠ ህፃን ነው፤ በየጊዜው ትኩረት እና ክትትል ይፈልጋል፣

👉 የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ውስንነት አለ፣ ፕሮጀክቶችን እኔ የመንግስት ቅጥረኛ ነኝ፣ ኮንትራክተር ነኝ ከማለት ወጥቶ ቤቴን ነው የምሰራው ብሎ በማስብ ፕሮጀክቶችን አሳምሮ የመስራት ውስንነት አለ፣

👉 መንግስት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመጨረስ ችግር የለበትም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፕሮጀክት ፍላጎቶች እና የመንግስት የማስፈፀም አቅም ላይ ችግር አለ፣

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ 346 የመንገድ ፕሮጀክቶች አሉ፣ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ወጭ የሚጠይቅ ከ26 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ፕሮጀክት እየተሰራ ነው፣

👉 የመብራት ማመንጫ፣ ማስተላለፊያ እና ማከፋፈያ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ፣ በመብራት ብቻ የ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላርፕሮጄክት አለን፣ የ5 ቢሊየን ዩሮ ፕሮጄክት አለን፣ የ110 ቢሊየን ብር ፕሮጄክት አለን፡፡

👉 በተጨማሪም የፌዴራል መንግስት ከ200 ቢሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ አነስተኛ እና መካከለኛ ግድቦችን እየገነባ ነው፡፡


👉 ትግራይ ክልል ባለፉት 30 ዓመታት በንፅፅር የተሻለ ሰላም ነበረው፤ በ30 ዓመት ውስጥ ግን ከስንዴ ልመና አልወጣውም፤ ካልሰራን ሰላም ብቻ ውጤት አያመጣም መስራት አስፈላጊ ነው፣

👉 የበጋ ስንዴ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የከተማ እርሻ እና ሌሎች የጀመርናቸው ስራዎች በከፍተኛ ደረጃ ከተረጂነት የሚያወጡ ናቸው፣

👉 ለክብራችን ስንል ከተረጂነት መውጣት አለብን፤ ተረጂነት ፖለቲካ ሳይሆን የኢትዮጵያ ክብር ነው

👉 አሁን ላይ በኢትዮጵያ የሚረዱ እና የተፈናቃሉ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ይገኛል፣

👉 ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት እና አስር ዓመታት ከውጭ እርዳታ መቀበል አታቆምም፤ ኢትዮጵያን ለመርዳት ቅን ልቦና ያላቸው ት/ቤት እና ሆስፒታል የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን ይገነቡልናል፤ እኛ ይቅር ያልነው የስንዴ እርዳታ ነው፣

👉 በብዙ መንገድ ይህ ጊዜ የኢትዮጵያ ጊዜ ነው፤ የምንመራው በዕቅድ እና በመሻት ነው፤ ሕልማችን የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን ማድረግ ነው፣

👉 በ2032 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቢያንስ ከአፍሪካ ሁለተኛው ኢኮኖሚ ይሆናል፤ በ2036 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከአፍሪካ የመጀመሪያው ኢኮኖሚ ይሆናል።


👉እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊን የቤት ባለቤት እንዲሆን ማሰብ መሻት ብዙ የሚቻል ጉዳይ አይመስለኝም፤

👉አሜሪካም እንደዛ አይቻልም፤ የሚቻለው ጉዳይ እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአቅሙ ለመከራየት ቢፈልግ የቤት አማራጭ እንዲያገኝ ማድረግ እንጂ ሁሉም ሰው 500 ካሬ ሜትር መሬት እየተከፋፈለ ቤት እንዲሰራ ማድረግ አይደለም ዋናው ዓላማ።

👉ሰው ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ የኪራይ ቤት ሲፈልግ እንዳያጣ ማስቻል ነው፤ ይሄ ችግር ነው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ። በኪራይም ቤት አይገኝም ከተገኘም ውድ ነው፤ ይህንን ችግር መፍታት በዘላቂነት የኑሮ ውድነት እያመጣ ያለውን ጫና ለመቀነስ ያግዛል።

👉እኛ በሚቀጥሉት 6 ዓመታት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶችን እንገነባለን ብለን ስናቅድ ስራው አሁን አልተጀመረም አስቀድመን በብረት፣ በሲሚንቶ፣ በመስታወት እና በሌሎች ዘርፎች ሰፋፊ ስራዎች እና ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል።

👉ከዚህ በተጨማሪ ከ1 ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ የሚገነቡ ባለሦስት ወለል ቤቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን እያስገባን እንገኛለን፤ እንደእነዚህ ዓይነት ሰፋፊ ዝግጅቶች እያደረግን ቆይተናል።

👉1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶችን ስንገነባ በድምሩ ከ3 ትሪሊየን በላይ ኃብት ይፈስበታል።

👉በጋዝ፣ በነዳጅ፣ በማዳበሪያ፣ በቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ እና በቤት ግንባታ የምንሰራቸው ስራዎች በአጠቃላይ ጨዋታ ቀያሪ ናቸው።

👉በሚሊየን ለሚቆጠሩ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥሩና በከፍተኛ ደረጃ ምርታማነት እንዲጨምር የሚያደርጉ ናቸው፤


👉 በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየው እርስ በርስ መጋጨት መብቃት አለበት የሚለው ትክክለኛ ሃሳብ ነው፣

👉 ኢትዮጵያ ደካማ ሆና በሁለት እግሯ መቆም እንዳትችል የሚሰሩ ሀገራት ባሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን የሀገራዊ ጥቅምን ለይተው ማወቅ ካልቻሉ፣ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለጠላት ፍላጎት ተላልፈው ከተሰጡ የተሟላ ሰላም ማምጣት ያስቸግራል፣

👉 የኢትዮጵያን እድገት እና ሰላም የማይፈልጉ ሀገራት በጦርነት ማሸነፍ እንደማይችሉ ያውቁታል፤ ለምን የኢትዮጵያን አቅም ላኪው ያውቀዋል ተላላኪው ግን ይጓጓል፣

👉 በተነገረው ቁጥር ዘሎ እዚህ የሚመጣ ስለሚመስለው ተላላኪው ይጓጓል፤ ጉጉት የወለደው በሽታ ነው፣ እየተላከ እንደሆነ እና በራሱ ዓላማ እንዳልቆመ እና ራሱ የያዘውን ሃሳብ ይዞ ቢመጣ ለውጥ እንደማያመጣ ያውቃል ግን ጉጉት ይይዘዋል፣

👉 ኢትዮጵያ ውስጥ የሆነን ሰፈር እገነጥላለሁ እጠቀልላለሁ የሚል ገቢር ነበብ አይደለም ኢትዮጵያ ለመገንጠልም ለመጠቅለልም አመቺ አይደለችም፣

👉 ይሕን ባለማወቅ በጉጉት እና በመሻት የሚጋለቡ ፈረሶች የእነሱን ፍላጎት ለማሳካት ቀላል መንገድ የሚመስላቸው ከጠላት ጋር ማበር ነው፣

👉 ብዙዎቹን ስንመለከት መገንጠልም መጠቅለልም ሲባል ሰምተው ነው እንኳን ለመጠቅለል አክብሮ ለመኖርም ጊዜው ከባድ እንደሆነ አልተረዱትም፤ ይህ ችግር ባለበት የተሟላ ሰላም ማምጣት ውጣ ውረድ አለው።


👉 ከታሪክ መማር ቢቻል ኖሮ በድፍን አፍሪካ መሳሪያ ይዘው መንግስታትን ተቃርነው አሸንፈው ልማት እና ዴሞክራሲ ያመጣ የለም፣

👉 ታጥቆ ይመጣል ታጥቆ ይመለሳል፤ ኢሕአዴግ 17 ዓመት ታግሎ መንግስት ከሆነ በኋላ ለ30 ዓመት ሰላም የነበረበትን ትግራይ ክልል እንኳን ከስንዴ ዕርዳታ መገላገል አልቻለም፣

👉 በመሳሪያ የሚመጡ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከመሳሪያ ያለፈ ነገር ማሰብ አይችሉም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ብቻ ነው የሚያስፈልገው በሰላም ለመሄድ ደግሞ ትዕግስት እና ጊዜ ያስፈልጋል፣

👉 እንደ መንግስት ችግር አለብኝ ከሚል የትኛውም ኃይል ጋር ተወይይተናል ለምሳሌ ሸኔ ጋር ተወያይተን ከፊል የሸኔ ኃይል ስልጣን ላይ አሉ፤ ከትግራይ ወገኖች ጋር ተወያይተን ከፊሎቹ ስልጣን ላይ አሉ፣

👉 እኔን እና ጌታቸው ረዳን በጋራ የተመለከተ ይህንን መንግስት አይወያይም ብሎ ማሰብ የሚያስገርም ነው፣

👉 በሀገር ፍላጎት እስከተግባባን ድረስ የግሉን ጉዳዮቻችን ቸል ማለት አለብን፤ መወያየት ያስፈልጋል፣

👉 ተላላኪዎች ታገልኩለት ለሚሉለት ህዝብ ማዳበሪያ እንዳይሄድ እያደረጉ፣ ልማት እያደናቀፉ፣ እየገደሉ ታገልኩልህ ማለት ምን ማለት ነው?

👉 ነባር ችግሮች አሉ፤ ህገመንግስት፣ ሰንደቅ ዓላማ፣ ወዘተ የምትሉ ሠዎች በእናንተ ፍላጎት ማድረግ አንችልም እንወያይ ህዝብ ይወስን ነው እኛ ያልነው፣

👉 እኛ ነን ሁሉንም ያጠቃለለ ሀገራዊ ውይይት ደፍረን እንወያይ ያልነው፤ በየትኛው ዘመን ነው ሲፋለም የነበረ ሰው ታርቆ ዓመት ሳይሞላው ሚኒስትር የሆነው?


👉 ኢትዮጵያ የተሻለ ቁመና ያላቸውን ተቋማት ፈጥራለች፣

👉 ባለፈው ዓመት የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሀገር ደረጃ 18 ደርሷል፤ በቅርቡ 3 የሚጨመር ሲሆን በዚህ ዓመት 100 ለመድረስ እንሰራለን፣

👉 መሬት፣ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ ንግድ ፍቃድ፣ ግብር ላይ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው፣

👉 የዛሬ 3 ዓመት ኢትዮጵያ ለፓስፖርት ፈላጊ ዜጎች ማቅረብ የምትችለው 270 ሺህ ነበር፤ በዚህ ዓመት 4 ሚሊየን ነው የምታቀርበው፣

👉 በኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እየተካሄዱ ያሉ ሪፎርሞች ውጤት እያመጡ ነው፣

👉 ዲጂታል በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያመጣው ለውጥ ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል፤ 55 ሚሊየን ሰዎች ሞባይል ባንኪንግ ይጠቀማሉ፣

👉 ጂኤስኤም ባወጣው ሪፖርት በ2028 የዲጂታል ቴክኖሎጂው 11 ቢሊየን ዶላር ገደማ ሀብት ያመጣል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለ1 ሚሊየን ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራል።


👉 ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ያለን ስርዓት የሚፈርስ አይደለም የሚያጠናክር ነው እንጂ፤ ምርጫን፣ በጀትን እና የወታደር እንቅስቃሴን የሚያስቆም ምክክር አንፈልግም፡፡

👉 መንግስት እንደመንግስት ስራውን እያከናወነ ግብዓት የሚሆኑ ሐሳቦች ይመጣሉ አልን እንጂ፤ መንግስት ስራውን አቁሞ፣ ምርጫ አቁሞ፣ በጀት ማፅደቅ አቁሞ፣ ፓርላማ ይበተን አላለም፡፡

👉 የሀገራዊ ምክከር ሂደቱ ከምርጫው በፊት ካለቀ እሰየው ግብዓት እንወስዳለን፤ ከዛ በኋላም ካለቀ ጥሩ ነገር ግን ምርጫውን የሚያስተጓጉል ነገር የሚፈጠር አይመስለኝም፡፡

👉 ሀገራዊ ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይካሄዳል፡፡

👉 መንግስት ምርጫውን ለማካሄድ በቂ አቅም አለው፤ ምርጫ የአንድ ፓርቲ ፍላጎት አይደለም የጋራ ነው፡፡

👉 ሐሳብ አለኝ በምርጫ መሳተፍ እፈልጋለሁ የሚል ፓርቲ በምርጫው መሳተፍ ይችላል፤ እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በፊት ከተደረጉት ምርጫዎች የበለጠ ግልፅ እና ተአማኒነት ያለው ነበር፤ 7ኛው ደግሞ ይሻላል፡፡

👉 ይህ ምክር ቤትም አሁን ያለው መልክ አይኖረውም ብዬ አስባለሁ፤ ብዙ ድምፆች ይገባሉ ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ፣

👉 እንደ መንግስት እና ፓርቲ አማራጭ ድምፅ የሌለው ፓርላማ እንዲኖረን አንፈልግም፤ ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ፣ ግልፅ እና ተዓማኒ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...