ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ነገ ለፖርላማዉ ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ፡፡

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀፅ 17 እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 81 ንዑስ አንቀፅ 1 እና 3 መሠረት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የፌዴራሉ መንግሥት ባለስልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈፃሚውን አካል አሠራር የመመርመር፣ የመከታተልና የመቆጣጠር ሥልጣን አለው፡፡

በዚሁ ሕገ መንግሥትና የምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ መሠረት 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን፣ 2018 ዓ.ም በሚያካሂደው 30ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተው የመንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዓመታዊ በጀት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

በተያያዘም ምክር ቤቱ ፣ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን እንደሚያፀደቅ ይጠበቃል፡፡

በስብሰባው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች፣ አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የሚገኙ ሲሆን የጉባኤው ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት ይተላለፉል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር...

ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ንፁህ ኢነርጂ ፈንድ አምስቱ አቅኚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተመረጡ

በምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በማሳደግ የስራ እድልን ለመፍጠርና...

ታላቅ የምስጋና እና የስጦታ መርሃ-ግብር ጥሪ!

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት 5 ዓመታት ላበረከቱት ከፍተኛና ታላቅ...

የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ

ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን...