በሀገራችን የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ውስጥ የተለያዩ ፊልሞችን ድራማዎችን እንዲሁም የመዚቃ ቪድዮዎችን በመስራት እና ለማህበረሰቡ በማቅረብ በመዝናኛው ዘርፍ የራሱን አሰተዋፅኦ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው በፀሎት ፊልም ፕሮዳክሽን ከአሸወይ ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር “ጥላህ ነኝ” የተሰኘ ተከታታይ ድራማ ሰርቶ በማጠናቀቅ የመጀመሪያውን ምዕራፍ ለሕዝብ አቀረበ።
ጥላህ ነኝ ልብ አንጠልጣይ የቤተሰብ ድራማ / ወንጀል ዘዉግ ሲሆንባለ 48 ክፍል 4 ምዕራፍና የ30 ደቂቃ የጊዜ ርዝማኔ ያለዉ ሲሆን ከ50 በላይ ተዋናዮች ሲተዉኑበት በ1.8 ሚሊዮን ብር በጀት መሰራቱ ተነግሯል።የቀረፃ ቦታዎቹም አዳማ ቢሾፍቱ እና አዲስ አበባ እንደሆነ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
በጓደኝነት ጥላ ተከልሎና ታሞ የቆየው በአምስት ጓደኛማቾች መካከል የሚፈጠረው የፍቅርና የስሜት ትስስር ሲፈነዳ የፈላጊና ተፈላጊ አለመገናኘት መረባበሽ እንዴት እንደሚፈርና ከችግሩ ለመዉጣት የሚደረገዉን ያላባራ ጥረትና የመፍትሄ መንገዶችን በዋነኛ ጭብጥነት የሚታይበት እንደሆነ የጥላህ ነኝ ተከታታይ ድራማ ደራሲ አዘጋጅና ዳይሬክተር የሆነዉ ወጣት ነብዩ በቀለ ለጋዜጠኞች ተናግሯል።
ሐሙስ ህዳር 11/03/2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ሲ ኤም ሲ በሚገኘዉ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሸን አዳራሽ የኪነ – ጥበብ ባለሙያዎች የድራማው ተዋንያን እና አባላት/Crew/ እንዲሁም በክብር የተጠሩ እንግዶች በተገኙበት ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
አሸወይና ፊልምስ ፕሮዳክሽን እየተለመደ የመጣውን መናኛ የፊልም ጣዕም ለመቀየር የፊልም ተሰጥኦ ባላቸው በአዳማ ወጣቶች የዛሬ ሁለት ዓመት ማለትም በ2016 ዓ.ም በባለራዕይ የአዳማ ወጣቶች አማካኝነት የተመሰረተ ሲሆን ለሁሉም አባላቱ ለስራም ለእቅድም የመጀመሪያ የሆነውንና አዲስ ምዕራፍ ከፋች የሆነውን ጥላህ ነኝ የተሰኘ ተከታታይ ድራማ በዛው ዓመት በመስራትና በማሳካት የፍሬው ጊዜ ላይ እንደሚገኙ የአዳማዉ ባማ ኢንተርቴይመንት ፍሬዎች ባለራዕይ የጥበብ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የፕሮዳክሽን ካምፓኒዉ
ልዩ ልዩ ማህበራዊ እሳቤዎችን ፣ ልማዶችን ፣ ፍልስፍናዎችን ፣ ባዮግራፊዎችን ፣ ባህሎችን እና የመሳሰሉትን በፊልም መልኩ በመሰነድ ለዚህ ትውልድ መዝናኛ ፣ መወያያና ማስተማሪያ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ደግሞ የዛሬን ቀለም በምስል የሚሰነድ ታላቅ የፊልም ካምፓኒ መሆን ዓላማዉ ነዉ።
በመጪዎቹ 10 ዓመታት ውስጥ ለሀገሬው የፊልም ተመልካች ከባህር ማዶ ፊልሞች ጋር ተወዳዳሪ ጥራት ያላቸው ሀገርኛ ፊልሞችን የሚያቀረብ ሚዲያ መፍጠር ዋነኛ ራዕዩ እንደሆነአዘጋጆቹአብራርተዋል።
“ጥላህ ነኝ”ልብ አንጠልጣይ የቤተሰብ ድራማ / ወንጀል ነክ እንዲሁም በድርጊት የተሞላ ተከታታይ ድራማ በሰንሻይን ሚዲያ ዩቱብ (sunshine media you tube ) በኩል የመጀመሪያ ክፍል የተጫነ በመሆኑ ድራማውን የተለቀቅበት link
ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሲሳይ መንግስቴ
