ጦርነቶች ሁሉንም ነገር ያሳጡናል – ፖፕ ሊዮ

Date:

ዓለም በዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች የታገዙ ጦርነቶች ሁሉንም ነገር የሚያሳጡ እና ሰዎች በጭካኔ እንዲሞቱ  የሚያደርጉ  መሆናቸውን የፖፕ ሊዮ 17ኛ ገለጹ።

ጦርነትን መምረጥ መሸነፍ ነው ያሉት ፖፕ ሊዮ፥ ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ እና ዓለም አቀፍ ሕግን ማክበር፣ ኃላፊነት መውሰድና መተግበር ይበጃል ብለዋል።

ዓለም አቀፍ ሕግ እና ሰብዓዊ ክብር እንዲጠበቅ የሚመለከታቸው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አካላት፤ በኃላፊነት ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ እንዲሰጡም ፖፕ ፍራንሲስ ይጥሩ እንደነበር አስታውሰዋል።

“ጦርነትን መምረጥ ሽንፈት ነው በሰላም የምናጣው ነገር የለም”።

“ምርጫችን ጦርነት ከሆነ ግን ሁሉንም ነገር እናጣለን” የሚለው የፖፕ ፒውስ 12ኛ አስተሳሰብ፤ አሁን ላለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ መድኃኒት መሆኑንም ጠቁመዋል።

ፖፕ ሊዮ ይህን ያሉት በእስራኤልና በኢራን መካከል ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት ወቅት ነው።

ebc

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...