ለ150 ሺህ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በበየነ መረብ ይሰጣል

Date:


ለ150ሺህ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ፈተናን በበየነ መረብ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።

በዘንድሮው ዓመት 150ሺህ ተማሪዎች በበየነ መረብ ለመፈተን ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ 3 ሺህ 222 ትምህርት ቤቶች የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጡ ሲሆን ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 936 ሺህ 624 ተማሪዎች መካከል 416 ሺህ 284 ተማሪዎች በ48 ሺህ 242 መምህራን ማጠናከሪያ ትምህርት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በ2016 ዓ.ም ምንም ተማሪ ከለሰለፉ ትምህርት ቤቶች መካከል 700 ትምህርት ቤቶች ተለይተው የአንድ ዓመት ሙሉ ድጋፍ በተለያዩ ዘርፎች እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል።

ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተመረጡ 294 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 783 ርዕሰ መምህራን፣ 19ሺህ 566 መምህራንና 3ሺህ 628 የአስተዳደር ሰራተኞች በአጠቃላይ 23ሺህ 977 የትምህርት ማህበረሰብ በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል።

በ2016 ዓም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገውንና ውጤት የተገኘበትን የማጠናከሪያ ትምህርት በስፋት ለመስጠት የንቅናቄ ሰነድ በማዘጋጀት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

በ2016 ዓም 674 ሺህ 814 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲው መግቢያ ፈተና ወስደዋል። ከዚህ 29ሺህ 727 ተፈታኞች በተመረጡ ቦታዎች በበየነ መረብ መፈተናቸው ይታወሳል።

ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ...

ንግድ ባንክ “ስታርፔይ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ሥርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ...

በኢትዮጵያ በካንሰር ከሚያዙ ሕፃናት መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት ህክምና አያገኙም

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በካንሰር ከሚጠቁ ከ6 ሺህ እስከ 8 ሺህ...