በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

Date:

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ።

በከተማዋ በአሁኑ ወቅት ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተነግሯል

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ለስራው ደህንነት የሚሰጠው ትኩረት በማነሱ የሚደርሰውን ከፍተኛ የህይወት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የተቀናጀ የግንዛቤ ማስጨበጥና የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ በሀገሪቱም ሆነ በአዲስ አበባ ከተማ የስራ ላይ ደህንነት ጉዳይ እንደ ሁለተኛ አጀንዳ መታየቱ፣ በግንባታ ሳይቶች ላይ ለሚጠፉ የበርካታ ዜጎች ህይወትና ለሚከሰቱ አካላዊ ጉዳቶች ዋነኛ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት ባለሙያዎች ማህበር ባዘጋጀው ዓለማቀፍ የኮንስትራክሽን ጤናና ደህንነት ኮንፍረንስ ላይ የተገኙት ኢ/ር ወንድሙ፣ ይህ ችግር ከግለሰብ አልፎ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያስከተለ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በከተማዋ በአሁኑ ወቅት ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸውን የገለጹት ዋና ስራ አስኪያጁ፣ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ዜጎች እንደሚሰማሩ ገልጸዋል።

በመሆኑም በእነዚህ ሳይቶች ላይ የሚደርሰው የጥንቃቄ ጉድለት በሰራተኞች ላይ ብቻ ሳይሆን፤ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎችና መንግስት በከፍተኛ ወጪ በገነባቸው መሰረተ ልማቶች ላይ ጭምር ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን አመልክተዋል።

ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም፣ የከተማ አስተዳደሩ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ፣  የባለሙያዎች ስምሪት፣ እንዲሁም ጥብቅ ቁጥጥርና ህጋዊ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል።

የግንባታ ደህንነትን መጠበቅ በሁሉም የስራ ቦታዎች ላይ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ ጥረቶች መጀመራቸውንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...

ከምስራቅ ወለጋ በአዲስ መልክ ተፈናቅለናል ያሉ ሰዎች በደብረ ብርሃን በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ

ከዚህ ቀደም ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በደብረብርሃን የመጠለያ ጣቢያ...