ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ ማራኪሽ ላይ በሚካሄደዉ ታዋቂ አፍሪቃዉያን የአመራር እና ቢዝነስ ጉባኤ ላይ መሆኑ ተዘግቧል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር፤ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ እና የቀድሞዋ የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ዶ/ር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ዘንድሮ በሚካሄደው 100 ታዋቂ አፍሪቃውያን የአመራር እና ቢዝነስ ጉባኤ በሞሮኮ ማራኬሽ ላይ ፤ ክብር እና እውቅና ከሚሰጣቸዉ ታዋቂ የአፍሪቃ መሪዎች እና ግለሰቦች መካከል ይገኙበታል።


ጉባኤዉ፤ በአህጉሪቱ እና ከአህጉሪቱ ዉጭ ባሉ ሀገራት መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ ዲፕሎማቶች እና ለውጥ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት እያደገ የመጣ ተሳትፎን ተከትሎ በማራኬሽ ሞሮኮ ከሰኔ 19 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2018 እንደሚካሄድ የዝግጅቱ አዘጋጆች አስታውቀዋል።


ይፋ በተደረገዉ ዘገባዉ መሰረት፤ በዳቭዳን የሰላም እና የጥብቅና ፋውንዴሽን እና በ100 በጣም ታዋቂ የሰላም ቁንጮ የአፍሪካ አጋሮች ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው ይህ ዓመታዊ ጉባኤ፤ ልህቀትን ለማክበር፣ ፈጠራን ለማራመድ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስፈን፣ ድንበር ዘለል አጋርነቶችን ለማጠናከር እና ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት የሚሰራ የአፍሪቃ ግንባር ቀደም መድረኮች አንዱ ነው።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ በሚታየዉ፤ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፤ በአማራና ኦሮምያ ክልሎች አሁንም በሚታየዉ ግጭት፤ እንዲሁም በትግራይ የሚታየዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት በአገር ዉስጥ እና ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ከፍተኛ ትችት ይቀርብባቸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ከምስራቅ ወለጋ በአዲስ መልክ ተፈናቅለናል ያሉ ሰዎች በደብረ ብርሃን በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ

ከዚህ ቀደም ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በደብረብርሃን የመጠለያ ጣቢያ...