ልዩ መለያ ኮድ የሌለው ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ላይ አይውልም

Date:

ልዩ መለያ ኮድ የሌለው ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከነገ ጀምሮ ሥራ ላይ አይውልም – ሚኒስቴሩ

ልዩ መለያ ኮድ የሌለው ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ አይውልም አለ የገቢዎች ሚኒስቴር፡፡

የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) ያለበት የማንዋል ደረሰኝ ከባለፈው ዓመት ታሕሣሥ ወር ጀምሮ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝም ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ላይ እንደማይውል ነው ሚኒስቴሩ አጽንኦት የሰጠው፡፡

በዚህ መሰረትም ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) ያለበት የማንዋል ደረሰኝ ብቻ ለአገልግሎት እንደሚውል ገልጿል፡፡

የሕትመት ጥያቄ አቅርበው የታተመላቸውን ደረሰኝ ያልወሰዱ ግብር ከፋዮች ደግሞ በሚከፍሉበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወይም በየታክስ ማዕከላቸው በመገኘት ደረሰኞቻቸውን እንዲረከቡ አሳስቧል።

በተመሳሳይ ግብር ከፋዮች እጃቸው ላይ የሚገኘውን የቀድሞ ደረሰኝ ለየታክስ ማዕከሎቻቸው በመመለስ የመልቀቂያ ሰነድ መውሰድ እንዳለባቸው አመልክቷል፡፡

መመሪያውን በማይተገብሩ አካላት ላይ ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ርምጃ እንደሚወስድም አስገንዝቧል፡፡
ኤፍ ኤም ሲ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...