መንግሥት የትግራይ ተፈናቃዮችን በአፋጣኝ ወደቀያቸው መመለስ አለበት ሲል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ

Date:

በትግራይ ክልል ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎችን መንግሤት በአፋጣኝ ወደቀያቸው መመለስ እንደሚገባው የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ትግራይ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አሳስቧል። በክልሉ ከሱዳንና ጠለምት ወረዳ ተመልሰው የመጡትን ሳይጨምር 970 ሺህ አካባቢ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ የገለጹት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ፀሀዬ እንባየ፤ በቂ ድጋፍም እየተደረገላቸው አለመሆኑን በሰጡት ቃል አስታውቀዋል።

የመጠለያ ድንኳንም  ከተሰራ ሦስትና አራት ዓመት አስቆጥሮ ያረጀ በመሆኑ፤ በጨርቅና ላስቲክ ሸፍነው እየተጠቀሙ እንደሚገኝም ገልጸዋል።አክለውም “የተፈናቃዮች አለመመለስ በትምህርት ስርዓቱና ሌሎች ማህበራዊ ሕይወቶች ላይ ችግር እየፈጠረ በመሆኑ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት አለበት” ብለዋል።

በመሆኑም ይህ ሁሉ ችግር ሊቀረፍ የሚችለው ግን ወደ ቀያቸው መመለስ ሲችሉ ብቻ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥተዋል።አሐዱም “የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) እርዳታ ማቋረጡን ተከትሎ በተለይም ተፈናቃዮች ላይ ምን አይነት ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል?” ሲል የጠየቀ ሲሆን፤ ኃላፊው በምላሻቸው ቀድሞውኑ የነበረው ችግር እየተባባሰ እንደሚሄድ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በእርዳታ ሰጪዎች አማካኝነት ለጥቂቶች ብቻ ድጋፍ ሲደረግ ለብዙሃኑ እንደተደረገ ተደርጎ መረጃ ስለሚሰራጭ ይሄ በራሱ ተፈናቃዮች ላይ ጫና ሲፈጥር የቆየ መሆኑን በማንሳት፤ በውጪ እርዳታ ተመርኩዞ የሚደረግ ድጋፍ ዘላቂ ስለማይሆን ዋነኛው መፍትሄ መንግስት በራሱ አቅም ማገዝ ሲችል እንደሆነም ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

@Ahadu

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...