የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
የቦርድ አባላቱን ሹመት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ተሿሚዎቹ በትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ባዳበሩት ክህሎት የድርጅቱን ተልእኮ ማሳካት የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ብሔራዊ ጥቅምን መረዳት የሚችሉ እንዲሁም ተቋሙን ለስኬት እንደሚያበቁ የታመነባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ፦
1፡- ብሌን ማሞ ……. የቦርድ ሰብሳቢ
2፡- ፈዲላ ቢያ ……. አባል
3፡- ተስፋዬ ዘውዴ ……. አባል
4፡- መሐመድ ካሳ ……. አባል
5፡- አፈወርቅ በደዊ ……. አባል
6፡- አስማ ረዲ ……. አባል
7፡- ዮናስ በቀለ ……. አባል
8፡- ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር ……. አባል
9፡- ኢሳያስ ካሳ (ዶ/ር)……. አባል ሆነው እንዲሾሙ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ መርምሮ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ተሿሚዎችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል።
