የአብነት ትምህርትን ተምረሃል፤ ይህ ትምህርት በሥነ ፅሁፍ ሥራዎችህ ላይ ምን አስተዋፅኦ አበርክቶልሀል?
ናርዶስ አለሙ (አ.አበባ)
ይስማዕከ፡- የአብነት ትምህርት እድሉን ላገኘ አእምሮ ወደላይ ምጥቀትን፣ ወደታች ጥልቀትን፣ ወደ ጎን ስፋትን ያጎናፅፋል፡፡ ከግልብነት (Shallow thinking) ይሰውራል፡፡ ከአጠቃላይ ትምህርቱ ባሻገር ህይወትን፣ አብሮ መኖርን፣ ፍፁም ወንድማማችነትንና መከባበርን ያለማምዳል፡፡ እንኳንስ የጥበብ ሥራን የየዕለት የቃላት ልውውጥን ቅኔያዊ ባህርይ ያላብሳል፡፡ የአብነት ትምህርትን ባልቀምስ ኑሮ ፀሐፊ የመሆን እድሌን እጠራጠረዋለሁ፡፡
በገድላትና በተአምራት መጻህፍት የተፃፉት ታሪኮች ኃይማኖታዊ አገልግሎታቸው ሲገለብ አስደናቂ የስነ ጽሁፍ ውጤቶችም ናቸው፡፡ እነሱን ማንበቤ ለታሪክ አወቃቀር፣ ለገፀ ባሕርይ አሳሳል፣ ለቃላት አመራረጥና ለወዘተርፈ አጥብቄ እንዳልቸገር ሳያረገኝ አልቀረም፡፡ በአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ ከመንፈሳዊው ህይወት መሳ ለመሳ
ለእውቀት፣ ለቅኔና ለጥበብ ትልቅ ቦታ ይሰጣል፡፡ ለእውቀት፣ ለቅኔና ለጥበብ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡት ልቦለዶቼም የዚሁ ነፀብራቅ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡
በርካታ ደራስያን በመፅሐፋቸው መግቢያ ላይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀርባሉ፤ ይስማዕከ ግን በአንዱ መፅሐፍ አንኳ ለፈጣሪ ምስጋና አላቀረበም፤ ለምን?
ሠለሞን ወልደመድሕን (ቤላ-አዲስ አበባ)
ይስማዕከ፡- በመጀመሪያው መጽሐፌ በ‘የወንድ ምጥ’ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረቤን አስታውሳለሁ፡፡ ሆኖም ይህ ለእግዚአብሔር ይበቃዋል ብዬ ትቼው አይደለም፡፡ ይልቁንስ የጠያቂዬን ያህል እግዚአብሔር ራሱ ለምን በየመጽሀፎቼ ገፆች ላይ እንዳላመሰገንኩት የሚቆጨው አይመስለኝም፡፡ ለምን ቢባል ይህ የምርጫና ከራስ ጋር የመግባባት ጉዳይ
ነው፡፡ እግዚአብሔርን ማመስገን የፎርማሊቲ ጉዳይ ወይም በእግዚአብሔር ማመንን የማስመስከሪያ ጉዳይ ወይንም በእግዚአብሔር የመሳለቂያ ጉዳይ መሆን የለበትም፡፡ ከልብ ከተነጋገርን እግዚአብሔር ሲፈጥረኝም እነዚህን ብቻ ሳይሆን አያሌ ሥራዎችን እንድሠራ መሆን አለበት፡፡ መሥራቴ አስደንቆኝ ሳይሆን ሥራዬን በሰጠኝ አእምሮ ስለሰራሁበት ማመስገን ይኖርብኝ ይሆናል፡፡ ይህንንም ለሰዎች የማሳወቅ ግዴታ የለብኝም፡፡ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የሚፀልዩት ግብዞች ተብለዋልና፡፡
በምትኖርበት ሐዋሳ በዓይነቱ የተለየና ለኪነ ጥበብ ሰዎች ከበሬታ የሚሰጥ ሆቴል መክፈትህ ይነገራል፤ እስኪ ውስጣዊ ይዘቱን በምናብ አስጎብኘን…
ይልማ ደጉ (ከአ.አበባ)፤ አቤ ከቤ (ከአሰላ)
ይስማዕከ፡- ልክ ነው፡፡ የቤቱ ስም ዣንዣድ ይባላል፡፡ በሀዋሳ ከተማ በአሞራገደል በኩል ወደ ሐይቁ በሚወስደው አውራ ጉዳና ላይ ይገኛል፡፡ መግቢያው ላይ እየተራመደ የሚያነብ ሀውልት ይገኛል፡፡ አለፍ ብሎ በመንኮራኩር ቅርፅ የተሠራ ፋውንቴን አለ፡፡ የፋውንቴኑ ውሃ የሚወርደው በመንከራኩሩ ላይ በታዘሉት ማስወንጫፊያዎች በሚገኘው ጭስ ማውጫ ነው፡፡ በውሃ የሚሰራ መንኮራኩር፡፡ ውሃው የሚያርፍበት የፋውንቴኑ ወለል የተገለፀ መጽሐፍ ነው፡፡ ከተገለፀው መጽሀፍ ላይ የተቀመጡ አዛውንት ሀውልት ይታያል፡፡ እርሳቸውም ከመንኮራኩሩ ሥር ሆነው ያነባሉ፡፡
ከጎናቸው የዴር 33 ሀውልት ይገኛል፡፡ በግቢው ዙሪያ የብዙ ታላላቅ ደራስያንና ፀሀፍት ስዕል በጥቁርና ነጭ ቀለም ተሰርቶ በፍሬም ተሰቅሎ ይገኛል፡፡ የማርክ ትዌይን፣ የዮሀንስ አድማሱ፣ የወሌ ሾይንካ፣ የፀጋዬ ገብረመድህን፣ የሼክስፒር፣ የስብሐት ገ/ እግዚአብሔርና የከበደ ሚካኤል ስዕሎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የውጪው ባር ላይ ተጠምዶ በሚንተገትግ መትረየስ ላይ ተቀምጣ ምታነብ ሴት ሀውልት አለ፡፡ በመትረየሱ ቀለሆች ውስጥ የወይን መጠጦች ተሰክተውበታል፡፡ በዛ አስከፊ ጫጫታና ጦርነት ውስጥም ማንበብ እንደሚቻል የሚገልፅ ሀውልት ነው፡፡ ወደ
ውስጥ ስንዘልቅ የውስጠኛው ባር በተሰበረ ብርጭቆ ቅርፅ የተሰራ ሆኖ በመስተዋት መደርደሪያ ላይ የውስኪ መጠጦች ተሰድረዋል፡፡ በውስጠኛው ግድግዳ ላይም የሌሎቹ ደራስያንና ፀሀፍት ስዕሎች ተሰቅለው ይገኛሉ፡፡ ካህሊል ጂብራን፣ በአሉ ግርማ፣ ዶስተዬቭስኪ፣ ሀዲስ አለማየሁ፣ ቻርልስ ዲከንስ፣ ወዘተ፡፡… ለቤቱ አጠቃላይ ይዘት ጥንታዊነትን ለማላበስ ጥረት ተደርጓል፡፡
ወደ ውስጥ ሲዘለቅ ጥንታዊነትን የተላበሰ ዋሻ ተገንብቷል፡፡ በውስጡም ፋኖስ
ተንጠልጥሎበታል፡፡ ከዚህ ባሻገር በዣንዣድ ውስጥ የሚከፈቱ ሙዚቃዎች የቆዩና ጥንታዊነትን የሚያስታውሱ ናቸው፡፡ ዣንዣድ ይህንን ይመስላል፡፡ ማስታወቂያ እንዳይመስል ብዬ ብዙ ላለማለት የተቆጠብኩ ይመስለኛል፡፡ በበኩሌ ለጥበብ
ቦታ ይሰጥ ዘንድ እንደአቅሜ ለመስበክ ሞክሬአለሁ፡፡ በቀጣይ ብዙ የሚሻሻሉ ነገሮችን በማሻሻል የሚጨመሩትን በመጨመር ቤቱን የበለጠ ጥበባዊ ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡ ላሁኑ ግን ባለው ነገር አልተከፋሁም፡፡
ዴርቶጋዳ መፅሐፍ በእንግሊዝኛ ሊታተም ነው፤ መታተሙ ምን ጥቅም አስገኘልህ? አሳታሚው ማነው? ተመራጭ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? ወደ ገበያ መቼ ይወጣል?
አክመል ሽፋ (ከደሴ)
ይስማዕከ፡- ዴርቶጋዳ “Unity Publishers” በሚባል አሳታሚ ድርጅት በእንግሊዝኛ ታትሟል፡፡ ሰሞኑን ከአንባቢያን ዘንድ ይደርሳል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ ሕንዶችና አሜሪካኖች ጥያቄ ቢያቀርቡልኝም ለሀገሬ አሳታሚ የፈቀድኩበት ምክንያት በቀጣይ የኛም ሀገር ስራዎች እየተመረጡ ተተርጉመው ለሌሎች ሀገራት አንባብያን እንዲደርሱና የባህል ወረራውንም ከመከላከል ወደ ማጥቃት ለማሸጋገር ነው፡፡ የዴርቶጋዳ በእንግሊዝኛ መተርጐም ጥቅሙ የእኔ ብቻ ሳይሆን ለስነጽሁፍ ከፍተኛ ቦታ ለሚሰጡ ሁሉ ነው፡፡ የሀገራችን ስነጽሁፍ ወደ ሌሎች ሀገራት ይደርስ ዘንድ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተተረጐመ ሲቀርብ አይስተዋልም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? ስነጽሁፋችን ለሌሎች የማይበቃ ርባና ቢስ በመሆኑ ነው? አይመስለኝም፡፡ የተነሳሽነትና ራስን አሳንሶ የማየት ችግር ይመስለኛል፡፡ እኛም ሀገር የምዕራባውያንን ሥራዎች የሚያስከነዱ ሥራዎች ጥቂት ይሁኑ እንጂ አሉ፡፡ የአንድ ሀገር ስነጽሁፍ ተተርጉሞ ለሌሎች ሲደርስ የስነ ጽሁፍ ምንጭ የሆነው ሀገር ባህል፣ ወግ፡ ታሪክ ፍልስፍናና ስነ ልቦናም ለሌሎች ይሰበካል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በምዕራባውያንም ሆነ በምስራቃውያን ከተፈፀመብን ወረራ ሁሉ የከፋ የሆነው ወረራ የባህል ወረራቸው ነው፡፡ ጦር ቢያዘምቱብን እንደማንሸነፍ ያውቁታል፡፡ በፅሑፎቻቸው ግን አጥብቀው ወረውናል፡፡ ታሪካችንን ለነሱ እንዲመች አድርገው ጽፈውታል፡፡ ይህም ለእውቀትና ለሀይማኖት ያለንን አክብሮት በመገንዘባቸው ነው፡፡ በስነጽሑፍ በኩልም ታላቅ ተፅዕኖ አሳድረውብናል፡፡ በአጸፋው እኛ ግን ተጠቃሽ እንቅስቃሴ አላደረግንም፡፡ ከዚህ አኳያ የዴርቶጋዳ መተርጐም ጥቅሙ ሀገራዊ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
የእንግሊዝኛው አርትኦት በአንድ አሜሪካዊ የስነፅሁፍ ምሁር ተሠርቷል፡፡ እኒህ የቱላኔ ዩኒቨርስቲ ምሁር የሆኑቱና ክሪስቶፎር ዌልስ የተባሉት ግለሰብ ዴርቶጋዳ ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጐም ለምዕራባውያን ባህል እንግዳ የሆነውን በማቅረብና ቋንቋውም እንዲሰምር አግዘዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያንም በአርትኦቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ደራሲው “ራማቶሓራ” መፅሐፍን ካጠናቀቀ በኋላ በሐዋሳ ከተማ ባልታወቁ ሰዎች መዘረፉን ተናግሮ ነበር፡፡ ጉዳዩ ለፕሮሞሽን የሚውል ማጯጯሂያ አይመስልም ወይ? ምናልባት ረቂቁ ቢኖር እንኳ በዚያ ፍጥነት መፅሐፉ እንደገና ተጠናቋል ማለትስ ለማመን አያቸስግርም?… ተዘርፈህ ከሆነ ከተሰረቅከውና ለሕትመት ከበቃው የትኛው ይበልጣል ትላለህ?
ፈቃደ ይበልጣል (ከባሕርዳር)
ድርሰትሕን ደህንነቶች ወሰዱብኝ ብለህ በጋዜጦች ሁሉ አውርተህ ነበር፡፡ እኔ ግን አላመንኩህም፤ እውነቷን ልትነግረን ትችላለህ? እሺ ደህንነቶች ከወሰዱብህ እንዴት አድርገህ ራማቶሃራን ፃፍክ? ቢወስዱብህስ ይሄን ያህል ማስጮህ ለምን አስፈለገ፤ አንዳንድ ሰዎች ለገበያ ነው ይላሉ፤ እውነት ነው?
ሀስና አወል (ከመሳለሚያ)
ይስማዕከ፡- ይህ የምፈልገውና እስካሁንም በሌሎች ሚዲያዎች ላይ ምላሽ ያልሰጠሁበት ጥያቄ በመሆኑ ጠያቂዎቼን አመሰግናለሁ፡፡ ጥያቄው ግን እርማት ቢጤ ያስፈልገዋል፡፡ እኔ “ደህንነቶች ወሰዱብኝ” ብዬ ተናግሬ አላውቅም፡፡ ወሳጁ ግለሰብ ይሁን ድርጅት አላውቅም፡፡ የራማቶሓራ መዘረፍ በኔ ውስጥ ጥሎት ያለፈ ከባድ ቁስል ስላለ ጥያቄውን
በዚህ መልክ ባልጠየቅም እመርጥ ነበር፡፡ ለፕሮሞሽን፣ ለማሟሟቂያ… የሚለው ጉዳይ አስገርሞኛል፡፡ ግምት እውነት አይደለም፡፡ ለዴርቶጋዳ አንድም ማስታወቂያ አልሰራሁም፡፡ ራማቶሓራንም እንደማስከትል ቀደም ብሎ በመታወቁ ከብዙ አንባቢዎቼ ያላሰለሰ ጥያቄ የማስተናግድበት ወቅት ነበር፡፡ አንድም ጥሩንባ ሳይነፋ ያለምንም ጂኒ-ጃንካ ያ ወቅት ስለኔ ስራዎች በየቦታው ውይይት የሚደረግበት ወቅት ስለነበር ተጨማሪ ማስታወቂያ አያስፈልግም ነበር፡፡ ስራዬን አጠናቅቄ ማቅረብን እንጂ በዚህ በኩል እንዲህ ዓይነት ማስታወቂያ ቢሰራ ምናምን ብዬ የማስብበት ጊዜም
አልነበረኝም፡፡ እንኳንስ ይህን ያህል ሴራ የማሴርበት ጫማዬን የማስርበት ጊዜ እንኳ ያጣሁበት ወቅት ነበር፡፡
የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መሆኔና ባለችኝ ትንሽ ቀዳዳ የምጽፍና ሌቱና ቀኑ የተደባለቀብኝ ሰው መሆኔ መዘንጋት የለበትም፡፡ የተሰጠኝ ቦታና ክብርም ይህንን ተራ ሁኔታ የሚያሳስበኝ አይደለም፡፡ መጽሐፌ በሰልፍ በሚሸጥበት ወቅት፣ ሕትመቱ አልዳረስ ብሎ በየማተሚያ ቤቱ በገባበት ወቅት፣ ከልቦለድ የራቀው አንባቢ ተመልሶ ለእኔ መጽሀፍ
ከበቂ በላይ በተሰለፈበት ወቅት እንዴት እንዲህ ዓይነት ክብረ ቢስ ማስታወቂያ ለመስራት እሞክራለሁ? አስተዳደጌም ይህን እንዳስብ አይፈቅድልኝም፡፡ ያሳደጉኝ ለሰማይ ለምድር የከበዱና የተከበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊነትን እንደ ሃይማኖት አስተምረውኛል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ውሸትን አይሰብክም፡፡ ሀሰትን አጭበርባሪነትን በድርሰቶቼ መፋለሜ መዘንጋት የለበትም፡፡ መጽሀፌን እንደተቀማሁ ለቅርብ ጓደኞቼ የሆነውን ነገርኳቸው፡፡ ፖሊስ ጣቢያ አስመዘገብኩ፡፡ በወቅቱ ከነበሩት ጋዜጦች በስልክ ጥያቄ ሲቀርብልኝም የሆነውን ሁሉ ነገርኳቸው፡፡ የገረመኝ ነገር ፖሊስ የሰጠው መልስ ነው፡፡ “የዘረፉትን ሰዎች ስለማያውቃቸው ለመከታተል አልቻልንም” ነበር ብለው ለጋዜጦች መልስ የሰጡት፡፡ የዘረፈኝን ሰው ባውቅ በሕግ አግባብ እከስ ነበር እንጂ ፖሊስን ፈልግልኝ እል ነበር እንዴ? አሁንም የሚታየው ነገር ይኸው ነው፡፡ ስንቱ በሚያብለጨልጭ ጩቤ እየተቃጣ ሞባይሉን ተነጥቋል? ስንቱ ጎኑ ተወግቶ
ኪሱ ተበርብሯል? ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ሲያስመዝግብ ግን “ታውቃቸዋለህ?” ይባላል፡፡ በበግነት የሚያስቅ ጥያቄ ነው፡፡ የኔም ነገር እንደዛው ነው፡፡
“ቢወሰዱብህስ ይህን ያህል ማስጮህ ነበረብህ?” ለተባለው ጥያቄ …እኔ
መዘረፌን ተናገርኩ እንጂ ዜናውም ያን ያህል ይጮሀል ብዬ አላሰብኩም፡፡ ከነጭራሹም ጋዜጦቹ ዜናውን ያወጡታል ብዬም አላሰብኩም፡፡ ቢጮህስ ዝርፊያንና ቅሚያን ማጋለጥ ተገቢ አይደለም? ምን ሲዘረፍ ነው በደንብ የሚጮኸው? ቁሳዊ ነገር? በወቅቱ ይህን አሉባልታ ስሰማ ከሰዎች ጋር ተገናኝቼ ለመነጋገርም ውስጤ እምቢ ስላለኝ ብቻዬን
አሳልፍ ነበር፡፡ ምናልባት አውቆ ነው… አልተወሰደበትም የሚለውን ወሬ ያናፈሱት ቀማኛዎቼም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ማንንም የጩኸቱን ልክ አልመጠንኩም፡፡ ብጮህም በወቅቱ ተጠቅቼ ስለነበር አልጠቀመኝም፡፡ የብቸኝነትና የአቅመ ቢስነት ስሜት አጥቅቶኝ ነበር፡፡ በዚህ ጥያቄ ውስጥ ሌላው የተነሳው ነገር “በዚያ ፍጥነት መጽሐፉን እንዴት
ጽፈህ አደረስህ?” የሚለው ነው፡፡ በወቅቱ እንደገለጽኩት የተወሰደብኝ በልቦለድ መልክ ተሰርቶ የተጠናቀቀው ረቂቅ አንጂ አጠቃላይ መረጃዎቼ ሁሉ አልተወሰዱብኝም፡፡ የተለያዩ ማስታወሻዎችና ወረቀቶች፣ የቪዲዮ ክሮችና ሌሎች መረጃዎች ነበሩኝ፡፡ እነዚህን አንደገና መበርበርና የቁጥርና የቦታ መረጃዎችን ማጠናቀር ነበረብኝ፡፡ የታሪኩን
ፍሰትና አጠቃላይ የመጽሐፉን መነሻ መሀልና መድረሻውንም የማውቀው ነው፡፡ የተወሰደብኝ ረቂቁ እንጂ ጥንቅላቴ አልነበረም፡፡ አሁንም ቢሆን የመጽሐፎቼ ታሪኮችና ደርጊቶች አእምሮዬ ውስጥ አሉ፡፡ ሌላው ጥያቄ “ተዘርፈህ ከሆነ
ከተሠረቅከውና ለህትመት ከበቃው የትኛው ይበልጣል ትላለህ?” የሚል ነው፡፡ ለህትመት ለበቃው ራማቶሓራ የበለጠ ፍቅር አለኝ፡፡ የስቃዬ ውጤት በመሆኑ መጽሐፉን ሳየው ራሱ ቁስሎቼና ድካሞቼ ይታወሱኛል፡፡ እንደገና በምጽፍበት
ወቅት እድሜ ልኬን የማልረሳቸው ገጠመኞችን አሳልፌአለሁ፡ መንገድ ላይ ስሄድ ራሱ እያሰብኩ ስለነበር ከየት ተነስቼ የት እንደደረስኩ ሁሉ ማስታወስ ያቅተኝ ነበር፡፡ በስህተት ቤቴ መስሎኝ እሰው ቤት ገብቼ ከማላውቀው ቤት ሳሎን መሀል ተገትሬ ተገኝቻለሁ፡፡ ሰዎች ግራ ተጋብተው ሲያፈጡብኝ ነበር ወደራሴ የተመለስኩት፡፡ የተሰጣ ልብስ ልወስድ የገባሁ ሌባ መስያቸው ነበር፡፡
መጽሀፉ ላይ ይህ ሁሉ ስሜቴ እንደይንፀባርቅብኝ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ ምንም ሆነ ምን ለጠላቶቼ ተንበርካኪ እንዳልሆንኩ ለማሳወቅ መጽሐፉን እንደገና ስጽፍ በሚጣፍጥ ስቃይ ውስጥ ሆኜ ነበር፡፡ ወገቡ ላይ ስደርስ የበለጠ እየቀለለኝ መጣ፡፡ የጠፋው ራማቶሐራ ባለ 33 ምዕራፍ ሲሆን እንደገና የተፃፈው ግን በ40 ምዕራፍ ነበር ያለቀው፡፡ የትኛው ይበልጣል? የጠፋው ሰብሰብ ያለና ውጥረቱ ሞቅ ያለ ነበር መሰለኝ፡፡ ይህኛው ደግሞ ከድርጊቶች ይልቅ ምልልሶች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ በጠፋው መጽሐፍ ላይ ኦንጎታ ለታዴዎስ ይቅርታ አታደርግለትም፡፡ እንደገና በተፃፈው ላይ ግን ይቅርታ እንድታደርግለት አድርጌያለሁ፡፡ ለህትመት በበቃው ራማቶሓራ ገጽ 285 ላይ “…..ይቅርታ፣ ይቅር ማለት የማይቻለውን ይቅር ማለት መቻል ነው፡፡ ….ይቅር
የማይባለውን ይቅር የሚል ሰው ከሰዎች ሁሉ የሰለጠነ ሰው ነው” ትለዋለች፡፡ መጽሀፉን እያገባደድኩት ስመጣ የእኔን ቀን ያበላሹትን ሰዎች ሳይቀር ይቅር በማለት ላይ ነበርኩ፡፡ ራሴን በትክክል የፈተንኩበት ወቅት ነበር፡፡ የመጽሐፉን የመጨረሻ አረፍት ነገር ስፅፍ፣ የአድያም መነፅር ሲሰባበር… አንዳች ስሜት ወሮኝ ነበር፡፡ እጄ እጅ
ሳይሰጥ የሰጠሁትን አጠናቀቀው፡፡ የመጀመሪያውን ራማቶሓራ ምጡዋን በተፈጥሮ አካሉዋ እንደተገላገለች እናት ወለድኩት፡፡ እንደገና የተፃፈውን ራማቶሓራ በኦፕራሲዮን ተገላገልኩት፡፡ ሁለቱም ያው ራማቶሓራ ነው፡፡ በኦፕራሲዮን መወለዱ በእናትየዋ አካል ላይ ቁስሉ ይቀራል፡፡ ሆኖም መወለዱ ግድ ነበር፡፡ እናትና ልጅ አብረው
መሞት የለባቸውምና፡፡
በርካታ መፅሐፎችን ለሕትመት አብቅተሃል፡፡ ለመፃፍ ምን አይነት ሙድ ይመችሃል?… አንድ መፅሐፍ ለማጠናቀቅ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅብሃል?
ሳራ ተክሉ (አዳማ)
ይስማዕከ፡- “ሙድ?” እኔ በየትኛውም ሰዓት መጻፍ እችላለሁ፡፡ አልቅምም! አላጤስም! ፈጣሪን እዚህ ጋ ላመስግን፡፡ ምንም ዓይነት ሱስ የለብኝም፡፡ ለዚህም ሙድ ምናምን ሳልል ባገኘሁት ሽርፍራፊ ሰዓትና ደቂቃ ሁሉ በየትኛውም ቦታ መፃፍ እችላለሁ፡፡ በያዝኩት ሀሳብ ላይ ለመመሰጥ በቂ ኃይል በየትኛውም ሰዓትና ቦታ ስላለኝ በቅጠልና በጢስ የሚጀበጅብ ሙድ፣ አድባር፣ ዛር፣ ገለመሌ የሚባል ነገር አላውቅም፡፡
“አንድ መጽሀፍ ለማጠናቀቅ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅብሀል?” ለተባልኩት መልሴ ቅልብጭ ያለና አጭር ነው፡- እጅግ በጣም አጭር ጊዜ፡፡ በያዝኩት ሀሳብ ላይ በየትኛውም ቦታ አምሰለስላለሁ፡፡ ማስታወሻ እይዛለሁ፡፡ በመረጃ የሚደገፈውን ሳልሰለች መረጃ እፈልጋለሁ፡፡
በጠረጴዛ ዙሪያ ከሀሳቦቼ ጋር ስቀመጥ ግን ጣራና ግድግዳ አልመለከትም፡፡ ወረቀት ላይ አፈሰዋለሁ፡፡ ስጨርስ ደጋግሜ አነበዋለሁ፡፡ የቋንቋና የታሪክ መፋለስ እንዳይኖረው አርመዋለሁ፡፡ ይኸው ነው፡፡ እኔ አንድ መጽሐፍ ለሀያ ለሰላሳ አመታት ተፃፈ ሲባል እገረማለሁ፡፡ እንዲህ የተባለለት መጽሀፍ ሲገለጥ እንጨት እንጨት የሚል ሆኖም
ሊገኝ ይችላል፡፡ ብዙ ታላላቅ መፃህፍት በአጭር ጊዜ የተፃፉ ናቸው፡፡ ወደ ፀሀፊያቸው የመጣው መንፈስ ሳይበርድ ስለሚፃፍ ሕይወት አላቸው፡፡ መጠቃቀስ ይቻላል፡፡
“የራሴላስን” ያህል ድንቅ መጽሀፍ የተፃፈው ለቀብር ማስፈፀሚያ ነው፡- በቀናት ውስጥ፡፡ ሼክስፒርም እጁና አእምሮው እኩል የሚሰሩለት የሚባልና በፍጥነት በመፃፍ የሚታወቅ
ነው፡፡ ፀጋዬ ገብረ መድኅንም በአንድ ሌሊት አንድ ቲያትር ጽፎ የሚያድር የሚባል ፈጣን ጸሀፊ ነው፡፡ የጥበብ ሥራ በተለይም የሥነ-ፅሁፍ ሥራ በሆነ ሀሳብ የመነቃቃት ጉዳይ ነው፡፡ መንፈሱ ሳይበርድ እስከሙቀቱ ለማስቀረት ፀሀፊው ስሜቱንና አእምሮውን አስተባባሮ በማተኮር መከተብ የሱ ፋንታ ነው፡፡ መቶ አመት ፈጀብኝ ማለት ከወሬ ፍጆታ አያልፍም፡፡
የመፅሐፍሕ ጭብጦች ኢትዮጵያዊ ቢሆኑም የታሪክ መሰናስሉ ከውጪ ደራሲያን የተቀዳ ነው የሚል ትችት ይቀርብብሃል፤ ለምሳሌ “ዴርቶጋዳ” የዳን ብራውን ድርሰት ከሆነው ዳቪንቺ ኮድ የተኮረጀ የሚያስመስለው ብዙ ነጥቦችን በጋዜጣ አንብቤያለሁ፤ እንዲህ የሚሆነው የምታነባቸው የውጪ መፅሐፍት ተፅዕኖ ስላሳረፉብህ ነው ወይስ
በሌላ ምክንያት?
መኩሪያ ክብሩ (ከጆበርግ-ኢ-ሜይል)
ይስማዕከ፡- በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ላለመናገር ተቆጥቤ ነበር፡፡ ለየትኛውም ትችት ምላሽ የመስጠት ፍላጎት የለኝም፡፡ በጥያቄ መልክ ከቀረበልኝ ግን የመመለስ ግዴታ አለብኝና እኔም ተገቢውን ምላሽ ብሰጥ ማንም ቅር የሚሰኝብኝ አይመስለኝም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለስድባቸው ምላሽ ሲሰጣቸው የተሰደቡ ያህል ያማቸዋል፡፡ በእነሱ ቁንጽል የእይታ መነጽር ሌላውም ገድግዶ እንዲያይበት የሚያስገድዱ ሀያስያን ነን ባዮች አሉ፡፡ “ኮረጀ… መነተፈ… በኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ ውስጥ የገባ ቅሌት ወዘተ..” ብሎ የሂስ ጥበብን ባጎደፈ መልኩ አጉራ ዘለል ስድብ ላጎረፈብኝ ግለሰብ አንዳንድ ሀቁን የያዙ ሀያስያን ተገቢው ምላሽ ተሰጥቶታል፤ በቂ ባይሆንም፡፡ ረጅምና ተጠየቃዊ
ምላሽ የሚያስፈልጋቸውን እንቶ ፈንቶዎቹን በዚህች ገጽ ብቻ ሳይሆን በሰፊ ገጽ ላይ የሚሰጥባቸው ናቸው፡፡ የተሰረቀ ለማስመሰል የተጨነቀበት አቅም አንድ መጽሀፍ ለመፃፍ የሚያስችል ጉልበት ሳያወጣበት አልቀረም፡፡ ሆኖም የተባለው ሁሉ በቀላሉ ከምን የመነጨ እንደነበርና አንባቢውም ይህንን ተራ ስድብ ተጠይፎት በማለፉ ተገቢውን ምላሽ ያገኘው ይመስለኛል፡፡ ያፈረበትም እንደሆነ ብዙዎች ያምናሉ፡፡
ከመሰረቱ ዴርቶጋዳ ከthriller ዘውግ የሚመደብ በመሆኑ በዚህ ዘውግ ካሉ መፃህፍት ጋር በማነፃፀር እንዲህ ነው እንዲያው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንድ መጽሀፍ
ከአንድ መጽሀፍ ተገለበጠ ሲባል መታየት ያለባቸው አያሌ አላባዎች አሉ፡፡ የሜሮዳን ጥርስ ከዳን ብራውን ድድ ላይ ነቅየ አልተከልኩላትም፡፡ ከጭብጡ፣ ከይዘቱ፣ ከገፀ ባህርይ አሳሳሉ፣ ከፍልስፍናው… ወዘተ መታየት አለበት፡፡ ይህን ለማለት ደግሞ እጁን ታጥቦ ብዕሩን መጨበጥ ነበረበት፡፡ ለፃፈው ከስሜት ያልፀዳ ስድብ ግን ምላሽ የመስጠትም ሆነ በዝርዝር የመግባት ፍላጎት የለኝም፡፡ ገፅም አይበቃንም፡፡ በወቅቱ በቂ ባይሆንም ተገቢውን ምላሽ የሰጡ ጽሁፎች ወጥተዋል፡፡ ዘመናዊውን የልቦለድ አጻጻፍ ዘይቤ የመከተል ፍላጎት ቢኖረኝም በጉልህ ተፅእኖ አሳድሮብኛል ብዬ የማስበው ደራሲ የለም፡፡
እስካሁን ያነበብኩልህ “ዴርቶጋዳ” እና “ራማቶሓራ” ትረካቸው አጥሮ በፊልም መልክ ቢሰሩ ጥሩ አክሽን ፊልም እንደሚወጣቸው አምናለሁ፤ ወደፊልም ኢንዱስትሪው የመሻገር ሃሳብ የለህም ወይ?
ልዑል ሐድጉ (ከአክሱም)
ይስማዕከ፡- መልካም ሀሳብ ነው፡፡ እኔ ግን ያሁኑ ዝንባሌዬ ከፊልም ይልቅ ልቦለዶችን መጻፍ ላይ ነው፡፡ ከፊልም ስክሪፕት ወደ ልቦለድ መመለስ አዳጋች ነው፡፡ ልቦለድ ሲፃፍ ካሜራውም ምኑም በደራሲው ቃላት ላይ ነው፡፡ ልቦለድ የአንድ ሰው ምሉዕ መንፈስ ውጤት ነው፡፡ ፊልም ግን የአንድን ሰው ጥበብና የአእምዕሮ ምጥቀት የምናይበት ሳይሆን የጋርዮሽ ሥራ ነው- የብዙ ጥርቅሞች አቅምና ክህሎት ጭማቂ ነው፡፡
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ወደፊት ወደፊልሙ እገባ ይሆናል፡፡ ስገባም ጠብ የሚል ሥራ ይዤ መሆን አለበት፡፡ ለጊዜው ግን በጽሁፎቼ ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ፡፡ የዴርቶጋዳና የራማቶሓራ ሶስተኛ ክፍል ብዙ ትግሎችን የሚጠይቅ ሥራ በመሆኑ ትኩረቴ ለጊዜው እዚህ ላይ ነው፡፡ ዴርቶጋዳ ሶስትን ባለኝ አቅምና ጥረት ጥሩ አድርጌ ለማቅረብ በመትጋት ላይ ነኝ፡፡ ትኩረቴን ሌላ ሥራ እንዲነጥቀኝ አልፈለግኩም፡፡ መጽሃፎቼን ወደ ፊልም የመቀየር አቅሙ ያለው ድርጅት ካለ ግን ቢሞከር አልጠላም፡፡ በኛው ሀገር ልጆች ቢሞከር በተለይ የብዙዎች ደስታ ይመስለኛል፡፡
ወላጆችህ ያወጡልህን ስም ቀይረህ “ይስማዕከ” ብለህ የሰየምከው ራስህ ነህ ይባላል፡፡ የድሮ ስምህ ማን ነበር? ለምን መቀየር አስፈለገህ?
መሰለ አለሙ (ከሃገረማርያም-ቡሌሆና)
ይስማዕከ፡- ጠያቂዬን ይቅርታ ልጠይቅ፡፡ የቀድሞ ስሜን መናገር አልፈልግም፡፡ ያለመናገር መብቴን ስላከበሩልኝ አመሰግናለሁ፡፡ ስሞቻችን በአእዕምሮአችን ተፅእኖ ላይ
ያሳድሩብናል፡፡ በአመለካከታቸውና በተግባራቸው ስሞታቸውን የሚመስሉ ሰዎች አጋጥሞት የሚያውቅ ሰው ይኖር ይሆን? መፅሀፍም “እስመ ስሙ ይመርሆ ሀበ ግብሩ” ይላል፡፡ ስሙ ወደ ድርጊቱ ይመራዋል ማለት ነው፡፡ ስሞች ሲጠሩ ወደ ድምፅ ኢነርጂ (ኃይል) ይቀየራሉ፡፡ ይህ ሞገድ ብዙ ነገሮችን ይዞ ወደ እኛ ይመጣል፡፡ በድምጽ አሻራ የሚከፈቱ በሮችን ወደፊት እናይ ይሆናል፡፡ በቁጥር 3 ዴርቶጋዳ ይህን ጥበብ ይጠቀሙታል፡፡ ብዙ ነገሥታት ስማቸውን የሚቀይሩት ከዚህ ምስጢር በመነሳት ነው፡፡ ለምሳሌ ተፈሪ መኮንን-ኃ/ስላሴ፣ ካሳ ኃይሉ-ቴዎድሮስ ወዘተ…፡፡ ስሞች ወደቁጥር ይቀየራሉ፡፡ እሱን አሰራር እዚህ ላይ መዘርዘር ጠቃሚ መስሎ አልታየኝም፡፡ ገጽም ይገድበናል፡፡ እኔም በልጅነቴ ከዚህ በመነሳት ነበር ስሜን የቀየርኩት፡፡ …አሁን ሳስበው ትክክል ነበርኩ፡፡ ትክክለኛውን ስሜን ስለሰጠኝ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ይስማዕከ ማለት በግዕዝ ቋንቋ ይስማህ ማለት ነው፡፡ የልብህን ተምኔት ይፈፅምልህ ማለት ነው፡፡ ምርቃት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ወደ ቁጥር ሲለወጥ በትክክል እኔን የሚገልፀኝ ትንታኔ
ይገኛል፡፡
በመፅሐፍህ በተለይ በዴርቶጋዳ ላይ በርካታ የመቼት መፋለስና የሙያዊ ትንታኔ አገላለፅ ጉድለት ይስተዋላል፤ የሂዩስተን ነዋሪ የሆኑ አንድ ፀሐፊ ስለ አሜሪካ በተለይ ተመድ አካባቢ ስላለው ስፍራ የገለፅከው ፈፅሞ ከእውነት የራቀ መሆኑን ተችተው የፃፉትን አንብቤያለሁ፡፡ ስለውትድርና ሙያ የፃፍከውም እንዲሁ፡፡ ከተሰጠህ
ትችት ጥቂቱን ላስታውስ፡- “…ምግብ አብሳይ ሴቶችን አስገድደው የሚደፍሩ የሰንጥቅ ብርጌድ አባላት የሆኑ ወታደሮች ሜሮዳን አስገድደው ለመድፈር ሲሉ ሁለቱ ዶክተር ወታደሮች ይደርሱና ያስጥላሉ፡፡ እንዲያውም ዶክተር ሚራዥ የድምፅ ማፈኛ የተገጠመለት ሽጉጡን በወታደሮቹ ላይ ይመዝዛል፡፡ ሽጉጡን ደግሞ በውጊያ ውስጥ ከሞተ ጄኔራል ላይ መውሰዱን ይነግረናል፡፡ አንድ ጄኔራል በብርጌድ አቋም ከተደራጀ ጦር ውስጥ ምን ይሠራል?… ያ የጄኔራል መኮንን ቦታም አይደለም፡፡ “ይሁን” ቢባል እንኳን አንድ ተራ (ብሔራዊ ወታደር) ከአንድ ጄኔራል ሬሳ ላይ ሽጉጥ የሚፈታበትና መሣሪያውን ደብቆ ይዞ በሠራዊቱ ውስጥ የሚኖርበት ዕድል ሊፈጠር አይችልም፡፡ በዚያን ወቅት፡፡
“…ወደ ሱዳን እየተጓዙ ሳለ የደርግ ሄሊኮፕተር በአየር ላይ ይከታተላቸዋል፡፡ እናም ይደርስባቸዋል፡፡ ማምለጫ ባጡበት ሁኔታ ውስጥ እንደገቡም ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ሄሊኮፕተሩ በጠላት አየር መቃወሚያ ተመትቶ ሲነድ ታያቸው፡፡ አብራሪውም በዣንጥላ (ፓራሹት) ሲወርድ አዩት፡፡ የጦር ሄሊኮፕተር አብራሪ ሄሊኮፕተሩ በአየር ላይ ሲመታበት በፓራሹት እንደሚወርድ ለመጀመሪያ ጊዜ የነገረኝ ይኼ ደራሲ ነው፡፡”
እንደዚህ ዓይነት ስህተት እንዳለበት ተጠቅሷል፤ ስለማታውቀው ቦታና ጉዳይ ስትፅፍ አስቀድመህ መረጃ ማሰባሰብ አይጠበቅህም?
መቶ አለቃ ጠና አደመ (ከሃዋሳ)
ይስማዕከ፡- በዚህ ትችት ላይ ራሱ ግልፅ ስህተት ፈጦ ይታያል፡፡ ሽጉጡን ከሞተ ጄኔራል ላይ የወሰደው ሚራዥ አይደለም፡፡ ሃያሲ ነኝ ባዩ ሰውዬ ለትችት ከመፍጠናቸው በፊት በደንብ ቢያነቡት መልካም ነበር፡፡ ሽጉጡን ደብቆ ይዞት የነበረው ዣንጊዳ እንጂ ሚራዥ አልነበረም፡፡ በዚህች አንዲት አንቀጽ ውስጥ እንኳ ተቺዬ አለመሳሳት አልቻሉም፡፡ ሌላው ጄኔራሎች በመደበኛ ጦርነት ላይ የመታኮስ ኃላፊነት የለባቸውም፡፡ በመደበኛ አውደ ውጊያ (conventional war) ላይ እንደተራ ወታደር በእርግጥ አይፋለሙም፡፡ የአእምሮ ወይም የሂሳብ ጨዎታዎችን የመቀመር ግዴታ ግን አለባቸው፡፡ በድንገተኛ ሁኔታዎች ውስጥ ግን ራሳቸውን አጣብቂኝ ውስጥ ሊያገኙት ይችላሉ፡፡
እንኳንስ አንድ ጄኔራል መንግስቱ ኃ/ማርያም ራሳቸው ግንባር ገብተው የተፋለሙበት ወቅት እንደነበር መመስከራቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ ዣንጊዳ በሰራዊቱ ውስጥ የነበረው ድርሻ አልተገለጸም፡፡ የታሪኩ ፍሰት ወይም ሀዲድ የተዘረጋው ሚራዥ ላይ ስለሆነ የሌሎች ንዑሳን ገፀ ባህርያት የየዕለት ሁኔታ በሰፊው አይተነተንም፡፡ በውስጠ ታዋቂነት ግን ይታወቃል፡፡ ሌላው ከሄሊኮፕተር በፓራሹት መውረድ አይቻልም የሚለው ነው፡፡ በመሠረቱ የዝላዮች ልምምድ ሳይቀር በሄሊኮፕተር ላይ ይደረጋል፡፡ በተገቢ ርቀት እየበረረ ከሆነ በበር በኩል በመዝለል ዣንጥላውን መዘርጋት ይቻላል፡፡ እንኳንስ በጭንቅ ጊዜ! ይህንንም ማንም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ የሂውስተኑ ነዋሪ ተመድን ማየታቸው አጠራጥሮኛል፡፡ በዴርቶጋዳ ለተገለፀው ሁሉ በርካታ ጥናቶች አድርጌያለሁ፡፡ የቪዲዮና ፎቶግራፍ ካርታዎችን እንዲሁም የፅሁፍ መረጃዎችን በመያዝ ነው የሠራሁት፡፡ ለልብወለድ ቀርቶ ለታሪክ እንኳ ሊበቃ የሚችል ጥናት አድርጌ ነው የሠራሁት፡፡ ርቀቶችን ሳይቀር በተለያዩ ዘዴዎች በመስፈር ብዙ ተጨንቄያለሁ፡፡ ስንዝር የምታህል ርቀት እንኳ በቼልተኝነት አልተውኋትም፡፡ ለዛም ነው ዴርቶጋዳ እውነተኛ ታሪክ እንጂ ልብወለድ አይደለም ብለው ብዙዎች የወጠሩኝ፡፡ ለቁጥሮች፣ ለቦታዎችና ለጥቃቅን ኩነቶች ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠ ይህ ያረጋግጣል፡፡ “በርካታ የመቼት መፋለስ” ብሎ እነዚህን ከራስ የእውቀትና የግንዛቤ ማነስ የመነጩ ስህተቶችን ወደ ደራሲው ማምጣት ተገቢ አይደለም፡፡ “ከመዋጥ ማላመጥ” ይላል ያገሬ ሰው፡፡ ለትችት ከመፍጠን ንባብ ቢቀድም ጥሩ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ዋሽንግተን ዲሲ እንደሚኖር አስመስሎ ስራዬን አብጠልጥሎ ጋዜጣ ላይ የፃፈ ግለሰብ አዲስ አበባ ውስጥ አግኝቶኝ ብዙ ምላሾችን ከሰጠሁት በኋላ “እኔ ነኝ በብዕር ስም ዋሽንግተን
እንደሚኖር አስመስዬ የፃፉኩብህ፤ አሁን ጥያቄዎቼን ስትመልስልኝ ይህን እውነት እንዳጋልጥ ተገድጃለሁ” ሲል ይቅርታ ጠይቆኛል፡፡ ይህ ሰው ከአዲስ አበባ ውጪ ወጥቶ አያውቅም፡፡ እንኳን ዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያ ውስጥ ደብረዘይት ድረስ እንኳ ተጉዞ አያውቅም፡፡ በስነ ፅሁፍ ላይ ይህን ያህል ደባ ለመፈፀም ህሊናው እንዴት እንደፈቀደለት፣ ለምን ጥቅም ሲልስ ይህን እንዳደረገው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ብዕር የሚጨብጡ እጆች ከስሜትና ከሌላ ጥቅም ሲፀዱ ሙያዊ ሂሶች ስነ ፅሁፋችንን ያሳድጉታል፡፡ የኢትዮጵያን ስነ ፅሁፍ ያቆረቆዘውና እያስረጀ የሚጥለው የሙያዊ ሂስ አለመዳበር ነው፡፡ በተራ ስሜትና በግል ጥላቻ ተነሳስተው ቆንጨራ ይዘው በሚወጡ የስድብ መሀንዲሶችና ለሥነ-ፅሁፍ ተቆርቁረው የአንባቢውን ስነ ፅሁፋዊ እይታ በሚያሰፉ ሀያስያን መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡
የልጅነት አስተዳደግህ ምን ይመስላል? የአብነት ትምህርት ቤት ቆይታህን ጨምረህ ብታብራረልኝ…
መስፍን አዲሱ (ከባሕር ዳር)
ይስማዕከ፡- ያደግኩት በአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡ ገና አራት አመት ሳይሞላኝ ጀምሬ ከቤተሰቦቼ ተነጥዬ እዛው ነው ያደግኩት፡፡ እግዚአብሔር አእምሮዬን ከፍቶልኝ በልጅነቴ ብዙዎች ረጅም አመታት የሚፈጅባቸውን ትምህርት በአጭር ጊዜ አቀላጥፌያለሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ቅኔ መማሬ በህይወቴ ትልቁ ምዕራፍ ነው፡፡ አሁን ላለሁበት ሁኔታ ያበቃኝ እሱ ነው፡፡ ወደ ዘመናዊው የአስኳላ ትምህርት ቤት የገባሁት ግን ዘግይቼ ነው፡፡ አስኳላ ትምህርቱንም በተርም (በደብል) እያለፍኩ ዩኒቨርስቲ የገባሁት በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ትከታተል እንደነበረ ይታወቃል፤ ትምህርቱን ከምን አደረስከው? ወደፊት በሕክምና ሙያ የመቀጠል ሃሳብ አለህ ወይስ በድርሰት ብቻ?
ክፍሌ ወጂ (ከመርካቶ)
ይስማዕከ፡- ይህ አመት የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን አጠናቅቄ የምመረቅበት አመት ነው፡፡ ከወራት በኋላ እመረቃለሁ፡፡ በጤናው ዘርፍ ልስራ አልስራ አላወቅኩም፡፡ ነፍሴ ሌጣ ወረቀትና ብዕር ያምራታል፡፡ ተቀጣሪ ከሆንኩ ደግሞ ጊዜ አግኝቼ የምወደውን የድርሰት ሥራዬን ለመሥራት እንከን ይሆንብኛል፡፡ በነገራችን ላይ ጤናን የተማርኩት ለመቀጠር
ሳይሆን ለእውቀት ነው፡፡ ስለዚህ በድርሰቱ ነው መቀጠል የምፈልግ፡፡
የድርሰት ስራዎችህ ከሚታዩና ሊሆን ከሚችሉ ጉዳዮች ይልቅ በምናብ ብቻ በሚብሰለሰሉ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኩራሉ፡፡ ራስህን የፋንታዚ ድርሰት ፀሐፊ ነኝ ትላለህ ወይስ የሳይንስ ፊክሽን (ሳይንሳዊ ልቦለድ) አድርገህ ትወስዳለህ?
ሀብታሟ ታሪኩ (ከልደታ)
ይስማዕከ፡- ፋንታዚ ድርሰቶች እኮ ለድርጊቶች ምክንያት አያቀርቡም፡፡ በኔ ሥራዎች ውስጥ ግን ሊሆን የማይችል ነገር አላየሁም፡፡ ብዙዎቹ ሀሳቦቼ ከፃፍኳቸው በኋላ በአለም ዙሪያ ተሰርተዋል፡፡ ከዴር 33 እስከ ቀያዮቹ ወፎች መጽሀፎቼ ከወጡ በኋላ ተሰርተው በተለያዩ ሚዲያዎች እንደ አስገራሚ ዜና ሆነው ቀርበዋል፡፡ ሊሆን የማይችል ነገር ከፃፍኩት ውስጥ የለም፡፡ ለሁኔታዎች ሁሉ አመክንዮ የሚያቀርብ…(cause-effect) ያለው ልቦለድ ፋንታዚ ሲባል ስሞቼ አላውቅም፡፡ ለምናባዊ ፈጠራዎችም ምክንያት ከቀረበላቸው ፋንታዚ አይደሉም፡፡ ሳይንሳዊ ትንታኔ የቀረበባቸው ምናባዊ ፈጠራዎች እንዲህ ሲባሉ ስምቼም አላውቅም፡፡ የሀያስያን ሙያም እንደዚህ አይነቶችን ሁኔታዎች በማብራራት አንባቢውን አንድ ርምጃ ወደፊት መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ቅድም እንደተናገርኩት መጽሀፎቼ እንደእውነተኛ ታሪክ ተቆጥረው ልቦለድ አይደሉም የተባሉበት ምክንያት ለእያንዳንዷ ድርጊት ተጠየቃዊ ትንታኔ ስለሚያቀርቡ አይደለም? ፋንታዚን ምን አመጣው?
ስሜትህን በደንብ ገልጬያለሁ የምትለው በግጥምህ ወይስ በልብ ወለድ?
አለሜ ይቻልሃል (ከጋምቤላ)
ይስማዕከ፡- በሁለቱም ዘርፎች የገለጥኩት ይመስለኛል፡፡ በግጥሞቼ በኩል መቅረብ ያለበትን ሀሳብ በነሱ በልቦለዶቼም እንደዛው፡፡ ለግጥም የሚሆን ሀሳብ አለ፤ ለልቦለድ የሚሆን ሀሳብ አለ፤ ለቴአትር የሚሆን ሀሳብ አለ፡፡ በጥንቃቄ መመረጥ አለበት፡፡ ለዘፈን የሚሆነውን ግጥም ለማስለቀሻ ከማድረግ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
ዴርቶጋዳ መፅሐፍህ በሁለት የተለያዩ ሽፋኖች የታተሙት በምን ምክንያት ነው? የሁለቱ ሽፋኖች ትርጓሜስ ምንድነው?
ደቻሳ ደሜ (ከአምቦ)
የመጀመሪያው ሽፋን በወጣ በሳምንቱ አንዳንድ አሉታዊ ነገሮች ወደ እኔ መጡ፡፡ መጽሀፉን ሳያነቡት ገና ሽፋኑን አይተው ፈረዱበት፡፡ ከሃይማኖት ጋር ሊያያይዙት ከጀላቸው፡፡ ወዲያው ጀርባውን የሰጠ ሰው ያለበት ሽፋን ይዤ ወደ አሳታሚዬ ሂጄ አስቀየርኩት፡፡ ጀርባውን የሰጠው ሽፋን ፊቷን ከሰጠችው ሽፋን የተሻለ ሆኖ ተገኘ፡፡ተበሳጭቼ ነበር ጀርባውን እንዲሰጥ ያደረግኩት፡፡ በኋላ የበለጠ ሆኖ ተገኘ፡፡ ለካስ ለበጎ ነበር ያጉረመረሙብኝ፡፡ ጀርባውን የሰጠው ጎልማሳ ምስጢሩን ከፊትለፊቱ ላለው ሲደብቅ ባንጠለጠለው ባለጉጥ መስቀል በኩል እኛ እንድናየው ሆነ፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እንኳንም የመጀመሪያውን ሽፋን ተቃወሙኝ፡፡ የተሻለ እንዲሆን ነበር ለካ፡፡ በነገራችን ላይ በዴርቶጋዳ ላይ ያለውን ባለጉጥ መስቀል ወርቅና ብር አንጣሪዎች በዛው ቅርፅ እየቀረጹ ሲሸጡት አይቻለሁ፡፡ በወህኒ ቤት (በተለይም በሀዋሳ ወህኒ ቤት) ህይወታቸውን የሚገፉ እስረኞች ደግሞ በእንጨት እየቀረፁ በመሸጥ መተዳደሪያ ሲያደርጉት አይቼ ተደንቄያለሁ፡፡
መፅሐፍቶችህን በተመለከተ ከተሰጡህ አስተያየቶች በጣም አስገራሚ ናቸው የምትላቸውን ብትጠቅስልኝ? በጋዜጦችና መፅሔቶች የሚቀርቡ ሂሶችንስ እንዴት ትመለከታቸዋለህ?
ሳምሶን ፍፁም (ከተክለሃይማኖት)
ይስማዕከ፡- አንድ ማንም የሚረዳው ጉዳይ አለ፡፡ ስንቱ ፅፎ ሳይነበብለት የቀረ አለ? ስድብ አንኳ የናፈቀው ስንት አለ! በየትኛውም ጎራ በእኔ ላይ የሚሰነዘሩ ሂሶች ሊያስደስቱኝ ይገባል፡፡ ያስደስቱኛልም፡፡ ለእኔ ሥራ ትኩረት ሰጥተው የተቹኝንም ያመሰግኑኝንም ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ፡፡ እኔን በዓለማችን ላይ ካሉ ድንቅ ድንቅ ፀሐፍት ጋር አመሳስለው የወረፉኝ ራሳቸው ሳያውቁት ለእኔ ቦታ ሰጥተውኛል፡፡ እኔን ረስተው መጽሀፎቼን ብቻ ሲመለከቱ ግን ከእኔ ከወጡ በኋላ ሥራዎቼ የታሪካችን አካል መሆናቸውን ይገነዘባሉ፡፡ የሀገራችን ስነ-ፅሁፍ ከሌሎች ሀገራት የሚያንስበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ከሌሎች ሀገራት ቀድመን ስነ ፅሁፍን የጀመርንና የበለፀገ የጽሁፍ ታረክም ያለን ሕዝቦች ነን፡፡ ገና ገና ያልተፃፈባቸው ጉዳዮች፣ ባህሎች፣ አፈታሪኮች… አሉን፡፡ ሀገሪቷ የፀሀፊ እንጂ የሚፃፍ ሀሳብ እጦት የለባትም፡፡ ምዕራባውያን ደራስያን በዚህ ሰዓት የሚጽፉበት ጭብጥ አጥተው የሁሉም ደራስያን ስራዎች ማለት ይቻላል ተመሳሳይ እስከመሆን ዘልቀዋል፡፡ እነሱ እንጂ እኛ ሀሳብ ለቀማ ወደ እነሱ አንሄድም፡፡ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይሏል ይህ ነው፡፡ ራሳችን አሳንሰን ማየት የለብንም፡፡ እኔ
በበኩሌ ይህ አባዜ የለብኝም፡፡ ከዚህ አኳያ ራሱን አሳንሶ የሚያይ ሥራዎቼን በከንቱ ጭቃ ሲቀባቸው ዝም ማለት የለብኝም ነበር፡፡ ነገር ግን ምላሹ በሌሎች ያምራል ብዬ ትቼዋለሁ፡፡ ቃለ መጠይቅ እንኳ ተቆጥቤያለሁ፡፡ ይህ የእኔ ስራ አይደለም፡፡ ሀገራችን በጣት የሚቆጠሩ ይሁኑ እንጂ ጥሩ ጥሩ ሀያስያን አሏት፡፡ እንደነ የሻው ተሰማ፣ አስፋው ዳምጤ፣ አለማየሁ ገላጋይ፣ ገዛኸኝ ፀ. በሩቅ ይሁን እንጂ አብደላ እዝራን ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለመጪው ትውልድም መኖር መለማመድ አለብን፡፡ ያልተወለደው ደራሲም እንዲፅፍ ልንተወው ይገባል፡፡ ከዚህ በቀር በእኔ ላይ የሚሰነዝሩ ሂሶችን በፀጋ እቀበላለሁ፡፡ ጠቃሚም ነው፡፡ ነገር ግን በተራ ስድቦች አንባቢ ለመበተን የሚተጉትን ለሀገራችን ስነጽሁፍ ስንል ልንታገሳቸው አይገባም፡፡ ለእኔ የሚወረውሩት ድንጋይ የሌሎችንም አንባቢ ያስበረግጋል፡፡ ደህና ብቅ ያለውን አንባቢ ወደነበረበት ለሚመልሱና አብዮቱን ለመቀልበስ ቀይ ውዥንብር የሚነዙትን በነጭ ውሽንፍር እንመልሳቸው ዘንድ የአብዮቱ አደራ አለብን፡፡ (…ቀጭን ሳቅ) …ይህን ስል ግን
ጠቃሚ ጠቃሚውን ገንቢ ሂስ ከመቀበል አልቆጠብም፡፡ ሥራዬንም እንደ 97ቱ ምርጫ እንከን የለሽ ብዬ ልመፃደቅበት አልከጅልም፡፡ የጥበብ ሥራ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡
“ተልሚድ” የተሰኘ ድርሰትህ አቀባበሉ እንዴት ነበር? ሰሞኑን ለሕትመት የበቃው “ተከርቸም” መጽሐፍሕ ከቀድሞዎቹ ድርሰቶችህ በምን ይመሳሰላል? የጭብጥ መመሳሰል የሚንፀባረቅ አይመስልም?
ልዑል ሐድጉ (ከተክለ ሃይማኖት)
ይስማዕከ፡- ለተልሚድ ጥሩ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ አንድ ሃያሲ የፃፉት ፅሁፍ አስገርሞኛል፡፡ ተልሚድንና ሚራዥን እያነፃፀሩ የፃፉበት እይታ የሚገርም ነው፡፡ በህይወት ጥልቀት ተልሚድ ከሚራዥ እንደሚልቅ ፅፈዋል፡፡ ሰፊ ምርምር አድርገው ሳይቸኩሉ ላደረጉት ጥረት እይታቸውን ሳላደንቅ አላልፍም፡፡
ተከርቸም ገና ሰሞኑን መውጣቱ ነው፡፡ በኢሜል በምን ያገኘኋቸው አስተያየቶች መልካም ናቸው፡፡ እንደ መጀመሪያ ስራነቱ ለሰዎች አይመጥንም፤ ቢሆንም አንባቢዎቼ ስለኔ አጀማመር ያውቁ ዘንድ እንዲያነቡት እድል መስጠት አለብኝ ስል ነበር ያሳተምኩት፡፡ ነገር ግን ካሰብኩት በተቃራኒ ሆኖ አንባቢዎቼ ወደውታል፡፡ ከሌሎቹ ልቦለዶቼ የሚለየው ነጠላ ታሪክ እንጂ ውስብስብ ታሪክ ስለሌለው ነው፡፡ የሚፈትን ሴራም የለውም፡፡ ….ተከርቸምን እንደ አንድ ልቦለድ ከራሱና ከተነሳበት ጭብጥ ጋር ሲያነፃፅሩት በቂ ሆኖ አግኝተውታል፡፡ ለማንኛውም እኔ በዚህ ሰዓት ትኩረቴ በቁጥር ሶስት ዴርቶጋዳ ላይ ነው፡፡ የጭብጥ መመሳሰል የተባለው ከምን የተነሳ እንደሆነ አልገባኝም፡፡ ሁለቱ ተከታታዮች ማለትም ዴርቶጋዳና ራማቶሓራ ተከታታይ እንደመሆናቸው መጠን በአቢዩ ጭብጥ የመመሰሳሰል ግዴታ አለባቸው፡፡ ንኡሳን ጭብጦቻቸው ግን ይለያያሉ፡፡ ተልሚድና ተከርቸም ግን ከሌሎቹ በተለየ ጭብጥ አንስተዋል፡፡ እነዚህን ጭብጦች ለማመሳሰል ከተሞከረ የኢያን ራንድን ስራዎች ምን ልንላቸው ነው?
በሕይወትህ ሞክረህ ያልተሳካልህ ወይም ተስፋ የቆረጥክበት ጊዜ ነበር?
በሕሪያ ኑሩ (ከአዲስ አበባ)
ይስማዕከ፡- ገና ለአቅመ ተስፋ መቁረጥ አልደረስኩም፡፡ የተመኘሁት ሁሉ ይሆናል ብዬ የማምን ሞኝ አይደለሁም፡፡ የሞከርኩት ሁሉ ይሳካል ብዬም አልጃጃልም፡፡ ተስፋ የምቆርጥበት ጊዜም አልደረሰም፡፡ ገና በሃያዎቹ የምገኝ ወጣት ነኝ፡፡ ብዙ ለመሞከር እንጂ ለአቅመ ተስፋ መቁረጥ አልደረስኩም፡፡ በመሠረቱ በመሳካቱ ብቻ ሳይሆን በመሞከሬ የምደሰት ሰው ነኝ፡፡ ተሸናፊ መንፈስ የለኝም፡፡ ተሸናፊዎች ስልቹዎች ናቸው፡፡ ደስ የሚለኝ የኮሎምበስ ንግግር አለ፡፡ በአንድ ገጣሚ እንዲህ ተገልጦአል፡፡ “በሚያስገመግም ድምፅ በሚስፈራ ቃሉ
አላቸው ኮለምበስ ቀጥሉ ቀጥሉ
……… አሁንም ቀጥሉ”
ሰላማዊ ውቅያኖስን ለማቋረጥ ሲሞክር መርከበኞቹ እንመለስ እያሉ ሲያስቸግሩት የሚመልስላቸው ነው፡፡
የሕይወት ፍልስፍናህ ምንድነው?
የሺሃረግ ታዬ (ከአዲስ አበባ)
ይስማዕከ፡- “እያሻሻሉ መግፋት እየተሻሉም ወደፊት! ለተሻለ ህይወት” የሚል ነው፡፡ በየቀኑ መወለድ በየዕለቱ ማደግ፡፡ የንጋቷን ጮራ በደስታ መቀበል – የምሽቷን ጀምበር በሀሴት መሸኘት፡፡ በራስ ደስተኛ መሆን፡፡
“አበሻ ቅንድቡ ነው እኮ ሰማዩ
አብረው ይጠልቃሉ ዓይኑና ፀሐዩ” የሚል ግጥም አለህ፤ ምን ማለት ፈልገህ ነው?
ክንፈ አጋ (ከላፍቶ)
ይስማዕከ፡- እኛ ኢትዮጵያዊያን ፀሐይ ስትገባ በራችንን መቀርቀር የለብንም፡፡ እንደ ሌሎች አለም ነዋሪዎች የሥራ ባህላችንን ማጠንከር አለብን፡፡ ቀኑን በአሉባልታ ሌቱን በመኝታ ማሳለፍ የለብንም፡፡ 24 ሰዓት የሚሰሩ ድርጅቶች ስንት ናቸው? ከመሸታ ቤቶች በቀር እዚህ ሀገር ከፀሀይ ግባት በኋላ ምን ክፍት በር ይገኛል? ዓይኖቻችንና
ፀሐያችን እኩል እያንቀላፉ እንዴት ነው ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚነፃፀር እድገት ሊኖረን የሚችል? ለዛ ነው፡፡
በዴርቶጋዳ መፅሐፍ ውስጥ ኢትዮጵያዊ/ት ያልሆኑ ለምሳሌ ሻጊዝ፣ ሚራዥ፣ ዣንጊዳ፣ ሜሮዳ የመሳሰሉ ስሞችን አብዝተሕ መጠቀም ለምን ፈለግህ?
ኢያሱ አ. (ከማይጨው)
ይስማዕከ፡- ኢትዮጵያዊ ስም ሲባል የትኛው ነው? አበበ… በቀለ ወዘተ… ማለት ነው እንዴ? ከሰማኒያ በላይ ብሔረሰቦች ባሉበት ሀገር ነው የምንኖር፡፡ ብዙ አስገራሚ ስሞች አሉ፡፡ አልተጠቀምናቸውም፡፡ ስሞች ብሔርን ስለሚገልጹ በዴርቶጋዳ ውስጥ መጠቀም አልፈለግኩም፡፡ “አበበ” ብለው አማራ ሊባል ነው፡፡ “ቢቂላ” ብለው ኦሮሞ ሊባል ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ጣጣ ለገዛ ገጸ ባህርዬ የራሴን ስም ባወጣ አይሻለኝም? ወስከምቢያ ሙሉ ፍትፍት አይጠይቀኝ? ከመጽሀፉ አጠቃላይ ይዘት ጋርም አይሄድም፡፡ አንድነትን በሚሰብክ መጽሀፍ ውስጥ ሊያውም ከመላው ኢትዮጵያ ተሰባስበው ኢትዮጵያን ለመታደግ በተጠራሩ ጀግኖች መካከል በስም የዘር ልዩነታቸውን ማጉላት አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ በራማቶሓራ ውስጥ ግን ለጭብጡ ጠቀሜታ ሲባል በስሙ የተጠራ ገጸባህርይ አለኝ፡፡ እሱም ማርዬ ዋቆ ማርዬ ነው፡፡ ይኸውም በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ ኦሮሞዎች ብቻ ሳይሆን ሌሎች ኢትዮጵያውንም በየትኛውም ቦታ ተዘዋውረው መኖርም ሆነ መስራት እንደሚችሉ ለመግለጥ ነው፡፡ አባይ ዳር ቤቱን ከወንዙ ዳር ሰርቶ በአበባ ባጌጠ ግቢ ውስጥ መኖር ለአማራ ብቻ የተፈቀደ ሳይሆን ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ለማስገንዘብም ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ እነዚህ ስሞች የፈረንጅ ስሞችም አይደሉም፡፡ ስማቸውን ከውስጣዊ ባህርያቸው ጋር እንዲሄድ አድርጌ ወደ ቁጥር ቀይሬ በቀመር ነው ያወጣሁላቸው፡፡ አንባቢ ግዴታ ይህን ሁሉ ያውቅ ዘንድ አይገደድም፡፡ ኮድ ነው፡፡
ራማቶሐራ መፅሐፍ ላይ ዩኒቨርስቲ እግር እንጂ ጭንቅላት አያስፈልገውም ብለሀል፡፡ አንተ ይህን ልትሆን ትችላለህ ወይስ ትደግፈዋለህ ወይ?
ታዴዎስ መለስ (አ.አበባ)
ይስማዕከ፡- ባያቸው አስገራሚ ዝቅጠቶች የተነሳ ወልደ ህይወት የሚባለው ገፀ ባህርይ እንዲህ ሲል በዲያሪው ላይ ፅፏል፡፡ ሁኔታዎችን ላየ አያስብልም አይባልም፡፡ ወደ ዩኒቨርስቲ በእግሩ እንጂ በጭንቅላቱ ያልገባ ሞልቷል፡፡ ሀቅ ነው፤ ግን ይጎረብጣል፡፡ የእያንዳንዱ ገፅ ባህርይ አስተሳሰብ የደራሲው አስተሳሰብ ነው ማለት አይደለም፡፡ አንተ ይህን ልትሆን ትችላለህ? ወይስ ትደግፈዋለህ? የሚለው ጥያቄ ግን ፈገግ የሚያሰኝ ነው፡፡ እንዴት ልደግፈው እችላለሁ? እኔስ በእግር የገባሁ እመስላለሁ? (…ረጅም ሳቅ)፡፡
በዴርቶጋዳ መፅሐፍሕ አንድ ለማኝ ስለ መለስና ስለ መንግስቱ ስም የሚለምንበት ቦታ አለ፡፡ አንተ ራስህ ፖለቲከኛ ነህ? የፖለቲካ መፅሐፍትን ታነባለህ? ከሙዚቃ የማንን ነው የምትሰማው?
መንግስቱ ደማሙ (ከሳሪስ)
እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም፡፡ መጽሀፍ ከሆነ ግን እንኳን ስለ ፖለቲካ ስለ ማስቲካም ቢሆን ጠራርጌ አነባለሁ፡፡ እንደ አንድ ዜጋ ስለ መብትና ግዴታዬ እታገላለሁ፡፡ ለተደራጀ የፖለቲካ ኃይልም ሆነ ለአንድ ተራ ግለሰብ በክብሬ ላይ አልደራደርም፡፡ በኢትዮጵያዊነቴ ማግኘት ያለብኝን የሰብአዊም ሆነ ዲሞክራሲያዊ መብት እስከመጨረሻው እጠይቃለሁ፡፡ ሌሎቹም ለፍትሐዊነትና ለሙሉ ነፃነታቸው ይታገሉ ዘንድ እጽፋለሁ፡፡ ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዳይዘነጉትም አስገነዝባለሁ፡፡ ይህ ፖለቲከኛ ቢያስብል አያስጨንቀኝም፡፡ ገፀ ባህሪዬን ስቀርፀው ሰው ሰው ይሸት ዘንድ ቁመናውና አካላዊ ገጽታውን ብቻ ሳይሆን አመለከካቱና አዕምሮው የተሠራበትን ማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ አካባቢውንም እጽፋለሁ፡፡ አለበለዚያማ በምኑ እኔን ይመስለኛል? ምን ቁመቱ ለግላጋ ቢሆን የሚወክለውን ማህበረሰብ ይገልፃል? ወደድንም ጠላንም ስነ ልቦናችን የተሠራው ፍልስፍናችን የተበጀው ከምንኖርበት ሀገርና በውስጡ ከያዛቸው ማህበረሰቦች ኃይማኖታዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አመለካከት ጭማቂ ነው፡፡

መንግስቱ ደማሙ (ከሳሪስ) እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም፡፡ መጽሀፍ ከሆነ ግን እንኳን ስለ ፖለቲካ ስለ ማስቲካም ቢሆን ጠራርጌ አነባለሁ፡፡ እንደ አንድ ዜጋ ስለ መብትና ግዴታዬ እታገላለሁ፡፡ ለተደራጀ የፖለቲካ ኃይልም ሆነ ለአንድ ተራ ግለሰብ በክብሬ ላይ አልደራደርም፡፡ በኢትዮጵያዊነቴ ማግኘት ያለብኝን የሰብአዊም ሆነ ዲሞክራሲያዊ መብት እስከመጨረሻው እጠይቃለሁ፡፡ ሌሎቹም ለፍትሐዊነትና ለሙሉ ነፃነታቸው ይታገሉ ዘንድ እጽፋለሁ፡፡ ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዳይዘነጉትም አስገነዝባለሁ፡፡ ይህ ፖለቲከኛ ቢያስብል አያስጨንቀኝም፡፡ ገፀ ባህሪዬን ስቀርፀው ሰው ሰው ይሸት ዘንድ ቁመናውና አካላዊ ገጽታውን ብቻ ሳይሆን አመለከካቱና አዕምሮው የተሠራበትን ማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ አካባቢውንም እጽፋለሁ፡፡ አለበለዚያማ በምኑ እኔን ይመስለኛል? ምን ቁመቱ ለግላጋ ቢሆን የሚወክለውን ማህበረሰብ ይገልፃል? ወደድንም ጠላንም ስነ ልቦናችን የተሠራው ፍልስፍናችን የተበጀው ከምንኖርበት ሀገርና በውስጡ ከያዛቸው ማህበረሰቦች ኃይማኖታዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አመለካከት ጭማቂ ነው፡፡