ሩሲያ በዩክሬን በፈጸመችዉ ጥቃት አራት ሰዎች ሲገድሉ ሌሎች 25 ሰዎች ቆሰሉ

Date:

የዩክሬን ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ሩሲያ በፈጸመችዉ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት በኪየቭ አራት ሰዎች ሲገደሉ ቢያንስ 25 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ሞስኮ ኦፕሬሽኑ ከዩክሬን ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ጋር የተገናኙ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በኪዬቭ ለተሰነዘረው እርምጃ ምክንያት መሆኑን ተናግራለች፡፡

ከቆሰሉት መካከል የህክምና ባለሙያዎች፣ የነፍስ አድን ሰራተኞች እና አንድ የፖሊስ መኮንን እንደሚገኙበት አቃቤ ህግ ተናግሯል። ጥቃቱ ዳርኒትሲያ፣ ዲኒፕሮ፣ ዴስኒያስኪ፣ ፔቸርስክ፣ ሼቭቼንኪቭስኪ፣ ሆሎሲቪስኪ እና ስቪያቶሺንስኪን ጨምሮ በዋና ከተማው በርካታ ወረዳዎችን ያማከለ ነበር፡፡

ባለሥልጣናቱ እንዳስታወቁት 19 ከፍተኛ ሕንፃዎችን ፣ ኤምባሲን፣ መዋለ ሕጻናት፣ ነዳጅ ማደያ ዴፖ፣ ያልተጠናቀቀ የመኖሪያ ሕንፃ፣ በርካታ ተሽከርካሪዎች፣ ሱፐርማርኬት እና ነዳጅ ማደያ ጋር ተጎድተዋል። የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች እና የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች ጉዳት በደረሰባቸው ቦታዎች መሥራታቸውን የቀጠሉ ሲሆን፥ የመጨረሻው የሟቾች ቁጥር አሁንም እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ጦር ሀይሎቹ የረዥም ርቀት ትክክለኝነቱ የተረጋገጠ መሳሪያዎችን እና የኦሬሽኒክ ባሊስቲክ ሚሳኤል ስርዓትን እንዲሁም በሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከፍተኛ ጥቃት መፈጸሙን አስታዉቋል፡፡ሚኒስቴሩ ጥቃቱ ያነጣጠረው የዩክሬን ወታደራዊ ኢንዱስትሪን በሚደግፉ የድሮን ማምረቻ ተቋማት እና የኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ ያነጣጠረ ነው ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...