ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው አረፉ!

Date:

የሮም ፓትርያርክና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ የነበሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ማረፋቸውን ቫቲካን በይፋ አስታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በ2013 የቀድሞ ጳጳስ በነዲክቶስ 16ኛ ከሥልጣናቸው ከለቀቁ በኋላ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ሆነው ተሹመዋል።

የእርሳቸውን ማረፍ በተመለከተ ካርዲናል ኬቨን ፋረል በቫቲካን በኩል በላኩት የሐዘን መግለጫ ላይ “ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በከባድ ሐዘን ቅዱስ አባታችን ፍራንሲስ ማረፋቸውን ላሳውቃችሁ እወዳለሁ” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የካቶሊክ አማኞች ዘንድ ያላቸው ፍቅርና ተቀባይነት ከፍተኛ እንደነበር ይታወቃል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...