ሰአሊ ብሩክ የሺጥላ የብርሃን ለህጻናት ግብረ ሰናይ ድርጅት የክብር አምባሳደር ሆነ

Date:

ለበርካታ ህጻናት ህይወት መቀየር ምክንያት መሆኑን ያነሳው ሰአሊ ብሩክ የሺጥላ በተሰጠው ሀላፊነት ደስተኛ መሆኑንና የተጣለበትን አደራ ለመወጣት እንደሚሰራ ተናግሯል።

በዝግጅቱም ብሩክ ለብርሃን ህጻናት ግብረ ሰናይ ድርጅት በቀለማት ህብር ያሸበረቀ የስዕል ሥራውን በስጦታ አበርክቷል።

ድርጅቱ አካል ጉዳተኛ ህጻናትን እንዲሁም ልጃገረዶችና ቤተሰቦቻቸውን ተደራሽ የሚያደርጉ ድጋፎችን በማቅረብ የሚሰራ እንደሆነም ተገልጿል።
በተለይ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር፣ ሲዳማ ክልሎች እና መካከለኛው ኢትዮጵያ ለ30 አመታት ሲሰራ ቆይቷል።

በXነዚህ ጊዜያት ከ23 ሺህ በላይ ህጻናትን ሲያግዝ እንደነበረም ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የግጭት አፈታትና የሰላም ግንባታ፣ ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል፣ የስርዓተ ፆታ ማካተት እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማስወገድ ላይ ይሰራል።

ድርጅቱ ዩኒሴፍ፣ ላይት ፎር ዘ ወርልድ ከተሰኙ እና ሌሎች አጋር አካላት  የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚደረግለት ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...