በህንድ ድልድይ ተደርምሶ 15 ሰዎች ሞቱ

Date:

በህንድ በደረሰ የድልድይ መደርመስ አደጋ 15 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ፡፡

አደጋው የደረሰው በሀገሪቱ ጉጅራት በተባለ አካባቢ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የድልድዩ መደርመስ ምክንያት ባይጠቀስም፤ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ለመፈለግ የነፍስ አድን ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ሲነገር የድልድዩን መደርመስ ተከትሎ አራት ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀ ተገልጿል፡፡

የሀገሪቱ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ኮሚሽን በአደጋው የጠፉትን ሰዎች እና የሟቾችን አስከሬን እያፈላለግኩ ነው ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...