በመርጦ ለማርያም የአስተርዮ ማርያም  የንግስ በዓል በደማቅ ሁኔታ ይከበራል

Date:

‎የጥር አስተርዮ በዓል  ኃይማኖታዊ ይዘቱንና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቅ መቻሉን የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባለሙያ የሆኑት አንለይ ደረሰ  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ለበዓሉ ድምቀትና ውበት ከጽዳት ዘመቻ ጀምሮ እስከ ማስዋብ ስራዎችን በዘመቻ እየሰሩ እና እንግዶችን ለመቀበል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸው ተገልጿል ።

መርጦለማርያም በኢትዮጵያ ካሉ ገዳማት መካከል  ቀዳሚ ከሚባሉት መካከል መሆኗን እና በርካታ ተንቀሳቃሽ እና ቋሚ ቅርሶች ባለቤት መሆኗ ተገልጿል ።

ከባለፈው አመት ጀምሮ በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በሚፈለገው መጠን እንግዶች እየገቡ አለመሆኑ እና  ከዚህ በፊት እስከ ሃያ ሺህ እንግዶች ይገኙ የነበረ መሆኑ  ተነግሯል።

‎በዓሉ በየዓመቱ ከተለያዩ አካባቢ በሚመጡ ሊቀጳጳሳት እና አባቶች ተባርኮ በደማቅ ሁኔታ የሚከበር በመሆኑ ሁሉም ምእመናን በበዓሉ ቀን በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባለሙያ የሆኑት አንለይ ደረሰ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...