በሀገራዊ የምክክር ሂደት ውስጥ ከሚሳተፉ አመቻቾች መካከል 50 በመቶ ያህሉ ሴቶች እንዲሆኑ ጥምረት ለሴቶች ድምፅ ጠየቀ።
60 የሚደርሱ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችን ያቀፈው ጥምረቱ፤ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ የሴቶችን እኩል ተሳትፎ ሊያረጋግጥ ይገባል ብሏል።
ጥምረቱ 10 አንገብጋቢ የሴቶች አጀንዳዎችን ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማስረከቡን ያስታወቀ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ እነዚህን አጀንዳዎች በምክክር የመጨረሻ አጀንዳ ውስጥ እንዲያካትት ተጠይቋል።
4 ሺሕ ሰዎችን ያካትታል ተብሎ የሚጠበቀው ዋናው የምክክር ጉባኤ 50 በመቶ የሴቶች ተሳትፎን እንዲያረጋግጥም ጥምረቱ ጥሪ አቅርቧል።
