በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው ገለጹ

Date:

በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብና የመጠልያ እጥረት እንዳጋጠማቸው ተናገሩ፡፡

በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ግጭቶችና ጦርነቶች ሰበብ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ፡፡

በክልሉ የደቡብ ወሎ፣ የሰሜን ጎንደርና የሰሜን ወሎ አንዳንድ ተፋናቃዮች ከጊዜ ወደ ጊዜ የእርዳታና የመጠለያ ችግር እያጋጠማቸው እንደሆነ መናገራቸውን ተዘግቧል፡፡ ከተፈናቃዮቹ መካከል የምግብ እርዳታ ካገኙ እስከ 5 ወራት እንደሆናቸው የተናገሩ ስለመኖራቸውም ተገልጿል፡፡

የክልሉ አደጋ መከላክልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በበኩሉ የተፈናቃዮችን ችግር በዘላቂነት ለመመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን የጠቀሰ ሲሆን፤ የምግብ እርዳታ ለማድርግ 500 ሚሊዮን ብር መድቦ እርዳታ እያቀረበ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ በክረምቱ ወቅት የጎርፍ ሥጋት ሊኖርባቸው ይችላል ተብለው በጥናት ለተለዩ አካባቢዎች ለአደጋ መከላከል ሥራ የሚውል 145 ሚሊዮን ብር መመደቡንም አመልክቷል፡፡

(ዶቼ ቬሌ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...