በሞባይላችሁ የፍቺ እና የሞት ሰርተፍኬት አገልግሎት ማግኝት

Date:

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ነዋሪዎች  ባሉበት ቦታ ሆነው በሞባይል ስልካቸው የሚያገኙትን አገልግሎቶች ቁጥር እንደሚጨምር አስታውቋል።

ተቋሙ ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገው ዐዲስ አገልግሎት የከተማዋ ነዋሪዎች በሞባይል ስልካቸው መታወቂያቸውን ማሳደስ፣ የልደት ሰርተፍኬት ማውጣት፣ መታወቂያቸውን ከፋይዳ ጋር የማስተሳሰር፣ ያላገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ሰርተፍኬት የሚሉ 4 አገልግሎቶች ናቸው።

በቀጣይ በዚህ አገልግሎት የጋብቻ እና የፍቺ ሰነዶችን በሞባይል ስልክ ማመልከት የሚቻልበት አሠራር እንደሚጀመር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ዐዲሱ አገልግሎት ለአዲስ የከተማዋ ነዋሪ ተመዝጋቢዎች የሚሰራ አለመሆኑን ገልጸው   መሸኛ በማቅረብ መታወቂያ ለመውሰድ የሚፈልጉ ዜጎችም ወደፊት  አገልግሎቱን በእጅ ስልካቸው የሚያገኙበት አሠራር እንደሚጀመር ገልጸዋል።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ነዋሪዎች ባሉበት ሆነው በእጅ ስልካቸው የሚያገኟቸው 4 አገልግሎቶች ወረፋ የሚበዛባቸው እንደሆኑ ገልጿል።

ነዋሪዎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ካመለከቱ በኋላ ክፍያውን በቴሌብር እንደሚፈጽሙ ተገልጿል። የጠየቁት አገልግሎት ሲፈጸም በሚደርሳቸው መልዕክት ባመለከቱበት ወረዳ በመሄድ መረከብ ይችላሉ::

አሐዱ ራዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እስከ አምስት ዓመት እስራት የሚያስቀጡ የመረጃ ነጻነት አዋጅ ጸደቀ

ለ15 ዓመታት በስራ ላይ ከቆየው “የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት...

በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ማስጠንቀቂያ

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለና...

በበጀት አመቱ 22.9 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሠራ ነው

ከታቀደው 22 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ኩንታል እስካሁን  20...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...