በአቪዬሽን ዘርፍ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት አዲስ ስምምነት ተፈረመ

Date:

በኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዘርፍ ያለውን የሰው ኃይል ልማት ይበልጥ ለማሳደግና ዜጎችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ የትብብር ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱ የተደረገው በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ መካከል ነው።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ ይህ ትብብር የአየር መንገዱን የዳበረ የቴክኖሎጂና የሥልጠና ልምድ በመጠቀም ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያስችል ነው። በተለይም በሚኒስቴሩ ሥር በሚገኙ የሙያና ቴክኒክ ሥልጠና ተቋማት በኩል የሚሰለጥኑ ወጣቶች በአቪዬሽን ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸው እንዲረጋገጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ያለው የባለሙያዎች ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ፣ ስምምነቱ ኢትዮጵያውያን በውጭ የሥራ ገበያ ውስጥ ተመራጭ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል። በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በዚህ ስምምነት አማካኝነት የሚፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በበቂ ሁኔታ ለማግኘት እንደሚረዳውም ተመላክቷል።

ይህ ስምምነት በሀገሪቱ የሥራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍና የሰለጠነ የሰው ኃይልን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ረገድ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ በዕለቱ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...