በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን 20ኛ ዓመቱን ያከብራል

Date:

ፌደሬሽኑ የተመሰረተበትን የ20ኛ ዓመት ክብረ-በአሉን  ከሃምሌ 22  እስከ  ሃምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ጀምሮ በጀርመን – ፍራንክፈርት ከተማ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮችና የሙዚቃ ዝግጅቶች እንደሚያከብር ያስታወቀው  በሃርመኒ  ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

በዚህ ክብረ በዓል ላይ ከሠላሳ በማያንሱ ክለቦች መካከል ከሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮች ባሻገር፣ የሃገር ባህልን የሚያንፀባርቁ የሙዚቃ ድግሶች እንደሚኖሩ ተጠቁሟል፡፡

በየዓመቱ እንደሚደረገው ከኢትዮጵያ የሚሄዱ የስፖርት ክለቦች በእግር  ኳስ ውድድሩ  ላይ  እንደሚሳተፉ የተገለጸ  ሲሆን፤ 10 የሚደርሱ የሀገራችን ትላልቅ አርቲስቶች የሙዚቃ  ሥራቸውን እንደሚያቀርቡም ተነግሯል ፡፡

በፍራንክፈርት በሚካሄደው የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ ሥራቸውን ከሚያቀርቡ  አርቲስቶች መካከል አንጋፋው ድምጻዊ  ፀሀዬ ዮሐንስ ፣ ልጅ ሚካኤል ፣ ህብስት ጥሩነህ ፣ ብርሀኑ ተዘራና አዲስ ሙላት እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል፤ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌደሬሽን በ2025 በፍራንከፈርት ለሚያካሂደው የ20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልና ዓመታዊ  ፌስቲቫል፣ ኪንግሶሎ ፕሮሞሽን በጋራ ለመሥራት መስማማቱ በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን  የተመሰረተው እ.ኤ.አ በ1999 ሲሆን፤ ጠንሳሾቹ ከሦስት ቡድኖች፣ ማለትም ከኢትዮ ፍራንክፈርት፣ ከኢትዮ ሆላንድ እና ከኢትዮ ፍራንስ የተውጣጡ የስፖርት አፍቃሪዎች ናቸው፡፡  ስብስቡ በየአመቱ እያደገ መጥቶ በ2005 በአውሮፓ በፌዴሬሽን ደረጃ ለመመዝገብ እንደበቃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ፌደሬሽኑ በ20 አመታት ጉዞው ዛሬ ከ22 የአውሮፓ ከተሞች የተውጣጡ 40 የእግር ኳስ ቡድኖችን ያፈራ ሲሆን፣ 20 ቡድኖች በአንደኛ ዲቪዚዮን ሲጫወቱ፣ 20ዎቹ ደግሞ በሁለተኛ ዲቪዚዮን የተሰለፉ ናቸው ተብሏል።

በመግለጫው ላይ እንደተብራራው፤ ዓመታዊ ዝግጅቱ የእግር ኳስ ውድድር ብቻ ሳይሆን፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት የአውሮፓ አህጉር፣ ከህፃን እስከ አዛውንት በጉጉት የሚጠብቁት፣ ዘመድ አዝማድ እንዲሁም  ጓደኛሞች  የሚገናኙበት ማእከልም ነው።

በዚህ የፌደሬሽኑ 20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልና ዓመታዊ የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ የንግድ ተቋማት አብረው በመሥራት አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ አዘጋጆቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የምክክር ኮሚሽኑ መዝጊያ

የኦሮሚያ ክልል ያቃረበውን ቅሬታ የተመለከተው የአሸማጋይ ቡድን አዲስ አበባ...

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...