በሪል ስቴት ዘርፍ ፈር ቀዳጅ የሆነው አያት ሪል ስቴት አክሲዮን ማኅበር፣ ከ18 ዓመታት በፊት በአያት ደራርቱ አደባባይ አቅራቢያ የገነባቸውን የመኖሪያና የንግድ ሕንፃዎች “የመጠቀሚያ ፈቃድ” ባለማስረከቡ ከ134 በላይ ባለንብረቶች ለከፍተኛ ቅጣት መዳረጋቸውን ገለጹ።
እንደ ባለቤቶቹ ገለጻ፣ ኩባንያው ሴፍቲ ታንክን ጨምሮ መሰረታዊ የሆኑትን የሊፍት፣ የውኃና የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ሳያሟላ በመቅረቱ የመጠቀሚያ ፈቃድ ሊከለከል ችሏል።
በዚህም ምክንያት የሞሉ ሴፍቲ ታንኮችን በራሳቸው ወጪ ለማስጠገን በሕግ ባለመቻላቸው በየጊዜው ለደንብ ማስከበር ቅጣት እየተዳረጉ መሆኑን በመጥቀስ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
በአንጻሩ አያት ሪል ስቴት ለችግሩ መዘግየት በምክንያትነት ያቀረበው ከዲዛይን ውጭ ለተሠሩ ሥራዎች ከግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የሚጠበቅ ምላሽ መዘግየቱን ነው።
