በእስራኤል ጥቃት የኢራኑ ፕሬዚዳንት መጠነኛ ጉዳት

Date:


የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በደህንነት ስብሰባ ላይ በነበሩበት ሰዓት እስራኤል በሰነዘረችው ጥቃት አነስተኛ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ተገለጸ፡፡

በፈረንጆቹ ሰኔ 17 የኢራን ከፍተኛ መሪዎች በተሰባሰቡበት ወቅት ጥቃት ሳይደርስባቸው እንዳልቀረ የሚጠቁም ሰነድ የኢራን ሚዲያዎች አግኝተናል በሚል እየዘገቡ ነው፡፡

ሾልኮ የወጣ ሰነድ ስብሰባው በምስጢር በምዕራባዊ ቴህራን ሲደረግ እንደነበር ጠቁሟል፡፡

የኢራን ከፍተኛ የደህንነት ምክር ቤት ስብሰባውን ሲያደርግበት በነበረው ህንጻ ላይ የስድስት ጦር መሳሪያ (ሚሳዔል) ውርጅብኝ ወርዷል ሲል ፋርስ ኒውስ ዘግቧል።

የህንጻው መግቢያና መውጫ ሲመታ ቀድሞውን ለአደጋ ጊዜ በተዘጋጀ መውጫ መሪዎችን ማዳን ተችሏል ፡፡

የእስራኤል ጦር በዋነኝነት የሄዝቦላህን መሪ ሀሰን ነስረላህን በገደለበት መንገድ የፈጸመው ጥቃት ነው ተብሏል፡፡

የምዕራቡ ዓለም ሚዲያ ይህን የሽብር ድርጊት አለመቃወሙንም የኢራን መገናኛ ብዙሃን እየተቹት ይገኛል ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ሪፖርቱ እንደሚጠቁመው ማሱድ ፔዜሽኪያን እግራቸው ላይ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ነበር፡፡

ከውስጥ ሾልኮ የወጣው ሰነድ ዝርዝር ጉዳዮችን ባያሳይም እስራኤል በመሪው ላይ ጥቃት ማድረሷን ጠቁሟል።

ፕሬዚዳንቱ ህይወታቸውን ቢያጡ እንኳን የቴህራን ፖለቲካ አይቀለበስም ነበር ተብሏል።

ቀደም ሲል ኢብራሂም ራይሲ ህይወታቸውን ቢያጡም “ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መሪ መርጠናል” በሚል የህዝባቸውን ጥንካሬም ለማስየት ሞክረዋል የኢራን ሚዲያዎች።

NBC Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ በቻይና ውይይት ያደርጋሉ 

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ወደ ቻይና የሚያደርጉትን መጪ ጉብኝት አስመልክቶ የክሬምሊን...

ከምዝገባ ካርድ ባሻገር፦ ለነገው ድምፅ የዛሬው ጥንቃቄ

ግዮን መጽሔት :- የምርጫ ካርድዎን በእጅዎ ይዘዋል? እንኳን ደስ...

በጤና አገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ የሕመምተኞችን ምስክርነት መጠቀም ተከለከለ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ...

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...