የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያየ ጊዜ በህጋዊ መንገድ የተፈፀሙ የይዞታ ግዥዎች የስመ-ንብረት ዝውውር እንዲደረግ ባስቀመጠው አስቀጣጫ መሰረት ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የስመ-ንብረት ዝውውርና የይካተትልኝን ጨምሮ ቀልጣፋ የመደበኛ አገልግሎት መስተንግዶ እየተሰጠ እንደሚገኝ የይዞታ ማስተካከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋሚካኤል እንዳለ ተናግረዋል፡፡
በውልና ማስረጃ ግዥ ፈፅመው የስመ ንብረት ዝውውር ያላደረጉ ዜጎች በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ ቢሮው ባመቻቸው የኦንላይን አገልግሎት በማመልከት እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ስመ በማዞር የንብረት ባለቤትነት ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ ዳይሬክተሩ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተቋም ደረጃ በተዘጋጀው የ90 ቀን ንቅናቄ በየደረጃው ከሚሰጡ መደበኛ የይዞታ አገልግሎቶች 660 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ያስታወሱት አቶ ተስፋሚካኤል በሰኔ ወር ብቻ ከ426 ሚሊየን 960ሺ ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
ጨምረውም በቀጣይ 30 ቀናት የስመ-ንብረትና ኢ-ካርታ አገልግሎትን ጨምሮ ከሌሎች የመደበኛ ይዞታ አገልግሎት 500ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ታውቋል።
