በዩክሬን የሰላም አስከባሪ ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ ስብሰባ ሊካሄድ ነው

Date:

በዩክሬን የሰላም አስከባሪ ጦር ጉዳይ ከ20 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት ከፍተኛ ወታደራዊ ስብሰባ ዛሬ በብሪታንያ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

በስብሰባው ላይ ብሪታንያና ፈረንሳይ በሚመሩት የሰላም ማስከበር ተልዕኮው ጥምረት የተካተቱ ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን÷ በዕቅዱ አተገባበር ዙሪያ በዝግ ይመክራሉ ተብሏል፡፡

በስብሰባው ላይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እና የአውሮፓ ህብረት እንደሚሳተፉም ተገልጿል፡፡

በምዕራባውያኑ ሀገራት የሚመራው በዩክሬን የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን የማሰማራት ዕቅድ ወደ ትግበራ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኬር ስታርመር ተናግረዋል፡፡

ፈረንሳይ እና ብሪታንያ ወታደሮቻቸውን ወደ ዩክሬን ለመላክ ፍቃደኛ መሆናቸውንና ሌሎች የጥምረቱ ሀገራት በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...