“በደስታዬም በሐዘኔም ግቢ ጉባኤ ከጎኔ ነበር ”

Date:

የጥቁር አንበሳ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚና ግቢ ጉባኤ ተማሪዋ ዶክተር ሜሮን ለገሰ።

ቅዳሜ መጋቢት 5 2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሕክምና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 263 የሕክምና ተማሪዎችን አስመርቋል።

በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከመላው ተመራቂዎች የላቀ 3.95 ውጤት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ለመሆን የበቃችው የጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ ተማሪ ዶክተር ሜሮን ለገሰ የዕለቱ ደማቅ ኮከብ ሆናለች።

የአምላኬ እገዛ ፣ይበልጥ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያኔ እንድቀርብ ያደረገኝ ግቢ ጉባኤ፣ የቤተሰብና የመምህራን ድጋፍ በተለይም በግቢ ጉባኤ ያገኘኋቸው ጓደኞቼ ለዚህ ክብር አብቅተውኛል ብላለች።

ግቢ ጉባኤ ውስጥ መሳተፌ ጊዜዬን የሚያጠፋብኝ መስሎኝ የነበረ ቢሆንም በተቃራኒው ይበልጥ ለጊዜ ያለኝ ትኩረት እና አጠቃቀም ፣ሰፊ ንባብና ከፍተኛ ትኩረት የሚጠይቀውን የሕክምና ትምህርት በብቃት ለመወጣት አግዦኛል ያለችው ዶክተር ሜሮን ለገሰ ሌሎች ተማሪዎችም በዚህ መንገድ እንዲያልፉ መክራለች።

ዶክተር ሜሮን ለገሰ በቀጣይ በተማርሁበት ቅድስት ቤተክርስቲያኔን እና ሀገሬን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ ነኝም ብላለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...