በዳሰነች ወረዳ 34 ቀበሌዎች ‘ሙሉ በሙሉ’ በኦሞ ወንዝ ሙላት ተጥለቀለቁ

Date:

በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በዳሰነች ወረዳ 34 ቀበሌዎች ‘ሙሉ በሙሉ’ በኦሞ ወንዝ ሙላት መጥለቅለቃቸውና 81 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች እና የመንግስት ኃላፊ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

“የኦሞራቴ ከተማ በውሃ ተከባለች፤ የጎርፍ መጥለቅለቁ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ከተማችን ሊገባ ይችላል፤ እጣፈንታችንን ቁጭ ብለን እየተጠባበቅን ነው” ሲሉ ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ በኦምራቴ ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል።

ሌላኛው ስሜ ባይጠቀስ ያሉ እና በጎርፍ መጥለቅለቁ ምክንያት ተፈናቅለው ነበረሙስ በተባለ መጠለያ ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪ በበኩላቸው፤ “የእርሻ ቦታዎችን ሁሉ ጠራርጓል። ቤቶችን አፍርሷል። ኦሞራቴ ከተማን ለመዋጥ ደግሞ አንድ ኪ.ሜ እንኳን አይሞላም የተቃረበው” ብለዋል።

ስማቸውም ሆነ የስራ ሀላፊነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኦሞራቴ ከተማ የመንግስት ሀላፊ፤ የኦሞ ወንዝ ሞልቶ የቱርካና ሀይቅ ከኦሞራቴ ከተማ ከዚህ ቀደም ከነበረው 60 ኪ.ሜ ርቀት አሁን ላይ ወደ 1.3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ መጠጋቱን ጠቅሰዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...