በጋምቤላ ክልል በጀት ዓመት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ2 ቢሊዮን በላይ ጭማሪ አሳየ

Date:


 
በጋምቤላ ክልል በበጀት አመቱ በተከናወነው የገቢ አሰባሰብ ዙሪያ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

በቢሮዉ የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ አቶ ሳሙኤል ገለታ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በበጀት አመቱ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ነበር።
 
በዚህም 5 .3 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል በማለት አቶ ሳሙኤል ገልፀው በተገኘው ውጤት  የእቅዱን 64 በመቶ አፈፃፀም ማስመዝገብ እንደተቻለ አስረድተዋል።

እስካሁን ድረስ በተሰበሰበው ገቢ ከ2017 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ2 ቢሊዮን በላይ ጭማሪ አሳይቷል።በዚህ ጊዜ  ውስጥ ጥሩ አፈፃፀም ተመዝግቧል ያሉት አቶ ሳሙኤል ይህን እውን ለማድረግ ለደንበኞች በሚሰጠው የአገልግሎት ጥራት ላይ ትኩረት በማድረግ የተለያዪ ስራዎች ተከናውነዋል ሲሉ አክለዋል።
 
በተለይም የህገወጥ ምርቶች እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ተጨማሪ ጥረት ተደርጓል በማለት የተናገሩት ቡድን መሪው በጉምሩክ ሥርዓት ማሻሻያ  መሰረት በርካታ ስራዎችን ማከናወን ተችሏል ሲሉ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...

የቶዮታ ኮሮላ መኪና በኤሌክትሪክ ሊመጣ ነዉ

የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ፤ እንደ ቴስላ እና...

ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች...

አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ የ10 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው

‎‎የሲዳማ ክልል ፍትሕ ቢሮ እንዳስታወቀው የቀድሞ የሲዳማ ክልል ሰላም...