“በ1500 ሜትር የተሻለ ሠዓት እያለኝ ለምን ተጠባባቂ እንደሆንኩ አልገባኝ”

Date:

✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከቀናቶች በፊት የቶኪዮ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳታፊ አትሌቶችና አሠልጣኞችን ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ በ1500 ሜትር ወንዶች አብዲሳ ፈይሳ ስሙ በተጠባባቂነት ተቀምጧል።

አብዲሳን ጨምሮ በርካቶች አትሌቱ የተሻለ ሠዓት እያለው ለምን ተጠባባቂ ሆነ?የሚል ጥያቄን በማንሳታቸውና IAAF በ1500 የተሻለ ሠዓት ያላቸው አትሌቶችን ዝርዝር ሲያስቀምጥ ከአትሌት ሠለሞን ባረጋ፣ከአትሌትኤርምያስ ግርማ ቀጥሎ ሶስተኛ ምርጥ ሠዓት እያለው ለምን ወደተጠባባቂነት ሊወርድ ቻለ?በተለይ ሠለሞን ባረጋ ወደ10ሺ የሚሄድ ከሆነ አብዲሳ ፈይሳ በሁለተኛ ምርጥ ሠዓትነት ሊያዝ ሲገባ ይሄ ያለመሆኑ ምክንያት ምንድነው?በማለት ጥያቄ እየመዘዙ ሲሆን በዚህ ዙሪያ የጉዳዩ ባለቤትስ ምን ይላል?እንደተባለው ተጠባባቂ በመሆኑ ቅሬታ አለው?የሚለውን በትክክል ለማወቅ ወደ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ የእጅ ስልክ በመደወል በዋትስአፕ አነጋግረነዋል።

አትሌቱ ስለ ጉዳዩ ሲያብራራ”ዕውነት ለመናገር ቅሬታ አለኝ፤3:34:67 እያለኝ ለምን በተጠባባቂነት እንደተያዝኩ እስከ አሁን አላወኩም፤ምክንያቱንም ይሄ ነው ብሎ የሚያስረዳኝ ሠው አላገኘሁም”በማለት አስተያየቱን የጀመረው አትሌት አብዲሳ ፈይሳ”ሲጀመር እኔ ሚኒማው አለኝ መቀመጥ የሚገባኝ ቦታ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው ደረጃ መሠረት በሶስተኛነት ነው፤በተለይ በ1500 ሜትር የተሻለ ሠዓት ያለው አትሌት ሠለሞን ባረጋ ወደ10ሺ ሜትር የሚሄድ ከሆነ ትክክለኛው ቦታዬ ተጠባባቂነት ሳይሆን በሁለተኝነት መቀመጥ ነው ያለብኝ”በማለት በጥያቄ የሚሞግተው አትሌቱ “ውጤቱን ይፋ ያደረገው አካል በምን መስፈርትና በምን ሲስተም አይቶ ወደተጠባባቂነት ሊያወርዱኝ እንደቻሉ እንቆቅልሽ ሆኖብኛል”ብሏል።

በቀጣይ ምን ለማድረግ እንዳሠበ በአስተያየቱ የቀጠለው አትሌት አብዲሳ “እኔ አሁን ከሀገር ውጪ ስፔን ነው ያለሁት፤በሆነው ነገር ቅሬታ ተሠምቶኛል፤እክከአሁን በጉዳዩ ዙሪያ ማንንም አልጠየኩም፤ወደ ሀገሬ እንደተመለስኩ ለምን ተጠባባቂ እንደሆንኩ እጠይቃለሁ፤የአምና ሠዓት ነው የሚያዘው ከተባለም በስፔን ናርጃ 3:32:37 አለኝ ይሄ ሠዓቴ ተጠባባቂ ሳይሆን ሁለተኛና ሶስተኛ ላይ ነው የሚያስቀምጠኝ፤ባለኝ ሚኒማ መሠረት ትክክለኛ ቦታዬ እንዲሠጠኝ በአካል ሄጄ እጠይቃለሁ”የሚለው አትሌት አብዲሳ

በአስተያየቱ በመቀጠል”ማመልከቻ ማስገባት አይጠበቅብኝም፤ምክንያቱም በተጠባባቂነት ስለተያዝኩ ጥያቄዬ በሠዓቴ መሠረት ትክክለኛ ቦታዬ ላይ ልቀመጥ ነው፤እግዚአብሄር ከፈቀደ ሀገሬን ወክዬ በአለም ሻምፒዮና ታሪክ መስራት ስለምፈልግ ተጠባባቂ መሆን አይገባኝም፤በሚኒማዬ መሠረት ነው መቀመጥ የሚገባኝ”በማለት የተናገረው አትሌቱ “ለምን በተጠባባቂነት እንደተቀመጥኩ ግን የሚያስረዳኝና በውስጤ የተፈጠረውን ቅሬታ በፍትሀዊ አሠራር የሚፈታ አካልን ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ እጠይቃለሁ”ብሏል በአስተያየቱ መጨረሻ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ።

አትሌት አብዲሳ በርቀቱ የተሻለ ውጤት ሊያመጣ ይችላል በሚል ከወዲሁ ተስፋ የተጣለበት ሲሆን በፔሩ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ላይ በ1500 ወርቅ በ5ሺ ሜትር ብር በማግኘት የሀገሩን ስም ያስጠራ የነገ የርቀቱ ተረካቢ የሆነ ወጣት አትሌት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...