ብሔራዊ ቡድን የ2027 ምድብ ማጣርያ ቅድመ ዝግጅትም እያደረገ ይገኛል

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታውን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር በመጋቢት ወር ያደርጋል። ይህን ጨዋታ በአሸናፊነት በመወጣት ወደ ምድብ ማጣርያ ለመሸጋገር ያለመ ቅድመ ዝግጅትም እየተደረገ ይገኛል።

ስኬታማ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት የክለቦች እና ብሔራዊ ቡድኑ ቅንጅት ወሳኝ በመሆኑ ተጫዋቾች በአካል ብቃትም ሆነ በስነ ልቦና ዝግጁ ሆነው በሚቀርቡበት ሁኔታ ዙርያ ከፕሪምየር ሊጉ ክለቦች ዋና አሰልጣኞች ጋር የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ዛሬ የተከናወነ ሲሆን ጥሪ ከተደረገላቸው የሃያው ክለብ አሰልጣኞች አምስቱ ብቻ ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መሪነት በተካሄደው ውይይት  የተጫዋቾች ጥሪ፣ የዝግጅት ሂደት እና በጨዋታው ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

በዛሬው ውይይት ላይ በጸሎት ልዑልሰገድ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ደግአረገ ይግዛው (ባህር ዳር ከተማ)፣ ጸጋዬ ኪዳነማርያም (መቐለ 70 እንደርታ)፣ ይታገሱ እንዳለ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ዳንኤል ጸሐየ (ምድረገነት ሽረ) በውይይቱ ላይ የተገኙ አሰልጣኞች ሲሆኑ ፌዴሬሽናችንም በዚህ መድረክ ላይ በመገኘት ለብሔራዊ ቡድናችን ግብአት የሚሆን ሀሳብ በማንሸራሸራቸው ምስጋናውን ያቀርባል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሪልስቴቶች ስማቸውን ማጽዳት አለባቸው”

"አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗን ዳግም ያረጋግጣል" ‹‹ሕዝባችን ማን...

“ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች”:-  ከዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል ጋራ ውይይት

ዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል በተለይ በ1997 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ 97...

የ12ኛ ክፍል የፈተና ቀን ታወቀ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሳልቫ ኬር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት...