ተርክዬ ከ1ሺህ በላይ ተቃዋሚዎችን እና ጋዜጠኞችን አሰረች

Date:

የኢስታንቡል ከተማ ከንቲባ ኢክሬም ኢማሞጉሉ መታሰራቸዉን ተከትሎ በተነሳ
ተቃዉሞ ከ1ሺህ1መቶ በላይ ሰልፈኞች እና የተወሰኑ ጋዜጠኞች መታሰራቸዉ ተዘግቧል፡፡

የፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ዋነኛ ተቃዋሚ የሆኑት ከንቲባዉ መታሰራቸዉን ተከትሎም ከ81 የቱርክ ግዛቶች በ55ቱ ተቃዉሞ ተቀስቅሷል፡፡

በአገሪቱ በቀጠለዉ ሰልፍ በቱርክ ታሪክ በዓመታት ከባድ ነዉ የተባለ ተቃዉሞ ተከስቷል፤ በዚህ ምክንያት የተደረገዉ እስርም ከዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ ከባድ ተቃዉሞ ገጥሞታል፡፡

ባለፈዉ ሳምንት በኢስታንቡል የተጀመረዉ ሰልፍ ወደ 55 የአገሪቱ ግዛቶች ተቀጣጥሏል፡፡ ተቃዋሚዎችም ከፖሊሶች ጋር ጭምር ግብግብ ዉስጥ የገቡበት መሆኑ ነዉ የተዘገበዉ፡፡

የ53 ዓመቱ ከንቲባ፤ ለዘመናት ተርክዬን እየመሩ የሚገኙትን ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃንን በምርጫ ማሸነፍ የሚችሉ ብቸኛ ሰዉ ተደርገዉ ይቆጠሩ ነበር፡፡
ከንቲባዉ፤ለ2028 ምርጫ ለመወዳደር የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ በመሆን በከፍተኛ ድምጽም ተመርጠዉ ነበር፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ ከኢራን ጋር የተስማሙባቸውን ነጥቦች ከአርብ በፊት ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙባቸውን...

‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ የመጽሐፉ ዓይነት፡-...

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...