ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ ለተጨማሪ 75 ቀናት እንደሚቆይ ተገለጸ

Date:

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክቶክን በአሜሪካ ውስጥ ለተጨማሪ 75 ቀናት እንዲቆይ የሚያስችል የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ መፈረማቸውን ማምሻውን አስታወቁ። ይህን ያደረጉት አስተዳደራቸው ቲክቶክ የአሜሪካ ንብረት እንዲሆን የሚያስችለውን ስምምነት ለመደራደር ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት እንደሆነ ተናግረዋል።

ትዕዛዙ ይፋ የሆነው የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት የመተግበሪያው ድርሻ በአብዛኛው ለአሜሪካ ባለሀብቶች ባለቤትነት ወደ ሚተዳደረው አዲስ የአሜሪካ ኩባንያ ለማሸጋገር ወደ ስምምነት እንደተቃረበ ፕሬዚዳንቱ በማመናቸው ነው።

የቻይናው ኩባንያ ባይትዳንስ ቲክቶክ ለአሜሪካ ባለሃብቶች ከተሸጠ በኋላ አናሳ ድርሻ እንደሚኖረው ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጭ ተናግረዋል።

ሆኖም ትራምፕ ቻይናን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ሰፊ ታሪፎችን ካወጁ በኋላ ቤጂንግ ስምምነቱን ሐሙስ ማቋረጧ ተገልጿል። የባይትዳንስ ተወካዮች ወደ ዋይት ሀውስ በመደወል “ቻይና የንግድ እና የታሪፍ ድርድር እስከሚጀምር ድረስ የቲክቶክ ሽያጭ ስምምነቱን እንደማትቀበል ገልጸዋል” የሚሉት ምንጩ፣ ቻይናና አሜሪካ በዚህ ዙሪያ በሚቀጥሉት 75 ቀናት ውስጥ ይደራደራሉ ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...