ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅን ለመጠበቅ የባህር ፖሊስ ተቋቋመ

Date:

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅን የሚጠብቅ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነ ‘የባህር ፖሊስ’  መደራጀቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የግድቡ መሰረተ ድንጋይ በመጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ከተጣለበት ዕለት ጀምሮ የፌደራል ፖሊስ በቦታው ያለው ሰላም እና የደህንነት ዋስትና  እንዲረጋገጥ የማድረግ ተልዕኮን እየተወጣ መሆኑን ረዳት ኮሚሽነር ሰለሞን ከበደ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ተናግረዋል፡፡

ሐይቁ 256 ኪሎ ሜትር ያክል የሚሸፍን በመሆኑ መደበኛ ሳይሆን ‘ኮስታል ፖሊስ ጋርድ’  በማቋቋም መጠበቅ ስላለበት ኃይሉ መደራጀቱን ገልፀዋል፡፡

በዚህም ከመከላከያ ኢንጅነሪንግ ጋር በመተባበር ጀልባዎችን የማዘጋጀት፣ የሰው ኃይል አደረጃጀቱን የማጠናከር እና የማሰልጠን ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በአካባቢው ላይ ስጋት እንደሌላ የገለፁት ረ/ኮሚሽነሩ ቅድመ መከላከል ስራ እንዲሁም ለግድቡ የሚውሉ ቁሳቁሶችን ማጀብ እየተከወነ ያለ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም  ከመንግሥት በሚሰጠው ተልዕኮ መሠረት ሥራውን በብቃት እንደሚወጣ ገልፀዋል።

etv

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...