በእርግጥ በኢትዮጵያ #ትምህርት ንግድ ነው፤ ለዚያውም የተጧጧፈ የቢዝነስ ስራ ነው ይባላል።
በተለይ የግል ተማሪ ቤቶች የንግድ ፈቃድ አውጥተው ወይም ከአምራችና አገልግሎት አቅራቢ ፈቃድ ጋር አጣምረው የሚሰሩት እንደሆነ ይሰማል።
ታዲያ ትምህርት የማህበረሰብ አገልግሎት መሆን ሲገባው እንዴት ወደ #ንግድ መስመር ሊገባ ይችላል? አካሄዱም ከዚህ መላቀቅ አለበት ተብሏል።
አቶ ደሳለኝ መኩሪያ ባለፉት 20 ዓመታት ከታች ከአንደኛ ደረጃ አንስቶ እስከ ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ በመምህርነት አገልግለዋል።
በትምህርት ቢዝነስ ስራና ኢኮኖሚ ውስጥም በአስተዳደር ጭምር ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል።
አቶ ደሳለኝ ትምህርት የማህበረሰብ አገልግሎት እንጂ የንግድ ፈቃድ ወጥቶበት የሚሸቀጥ ዘርፍ አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/2345632/
ሸገር 102.1
