ትራምፕን ስለጋበዝኩ የባህር ልምምዱን አዘግዩልኝ !

Date:



‎የቡድን 20 መሪዎችን ለማስተናገድ በዝግጂት ላይ የምትገኘዉ ደቡብ አፍሪካ በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ ዉሐ
‎ክልል የባህር ሀይል ልምምድ ለማድረግ ያሰቡት የቻይና እና የሩስያ የጦር መርከቦችን ወደ ሀገሪቱ እንዳይመጡና ስልጠናዉን እንዲያዘገዩት መጠየቋ ተነገረ ።

‎ በጆሃንስበርግ በህዳር 22 እና ህዳር 23 በሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንዲገኙ የዩ.ኤስ. ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ተጋብዘዋል ያለዉ የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ዲፓርትመንት ሃሙስ እንዳስታወቀው ሀገሪቱ
‎ለምታዘጋጀው ታላቅ ስብሰባ ደህንነት ሲባል ለጊዜውም ቢሆን ልምምዱ እንዲቆይ ለቻይና ጥያቄ አቅርቤያለሁ ብሏል ።

‎የ BRICS ቡድን መስራቾች የሆኑት ደቡብ አፍሪካ ከቻይና እና ሩሲያ ጋር በእየሁለት አመቱ የሚደረገው የጋራ የባህር ኃይል ልምምዶችን ሲደረግ የቆየ ሲሆን የዚሁ ስምምነት መሰረት ዘንድሮም በህዳር ወር መጨረሻ በቻይና መሪነት በደቡብ አፍሪካ ውሃ ላይ ለማድረግ እቅድ ተይዞ ነበር ።

‎የመከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ የባህር ኃይል ልምምዱን ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ለቻይና ያቀረበው ጥያቄ “ከደቡብ አፍሪካ G20 ፕሬዝዳንት ጋር በተያያዙ የሎጂስቲክስ ፣ የደህንነት እና ሌሎች ዝግጅቶች ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድሩ ለማረጋገጥ ነው” ብለዋል ።

‎በዚህ ስብሰባ ላይም የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በG20 ጉባኤ ላይ ከፈረንሳይ፣ ከጀርመን፣ ከእንግሊዝ እና ከሌሎች መሪዎች ጋር ሊገኙ ሲሆን የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ እንዲታሰሩ በሰጠው የአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ደቡብ አፍሪካ የፍርድ ቤቱን ህግ ፈራሚ በመሆኗ ትፈጽማለች ተብሎ ይጠበቃል።

‎የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በግንቦት ወር ከትራምፕ ጋር በዋይት ሀውስ በተገናኙበት ወቅት የዩኤስ ፕሬዝዳንት በ G20 ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ እንደነገሯቸው ቢገልፁም ነገር ግን ትራምፕ በደቡብ አፍሪካ በጥቁር የሚመራው መንግስት በሀገር ውስጥ ፀረ-ነጭ ፖሊሲዎችን እና ፀረ-አሜሪካን የውጭ ፖሊሲ አቋም በመያዝ በስብሰባው ላለመገኘት እንደሚያስብ በሐምሌ ወር ተናግሯል ሲል ያስነበበው AP የዜና ወኪል ነዉ ።


‎የኔታ ቲዩብ


ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...