ትራምፕ ለሶስተኛ ጊዜ አሜሪካ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች አሉ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ዕለት የሪፐብሊካን ሴናተሮችን በዋይት ሀውስ ተቀብለው ባስተናገዱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለት ሲናገሩ ተደምጠዋል።

“ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባችው በአብዛኛው በአሜሪካ ገንዘብ ነው” ሲሉ በአንድ ወር ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ተናግረዋል።

እውነታው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተገነባው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ህዝብ በህዝባዊ መዋጮ እና በአገር ውስጥ ሀብት መሆኑ ቢታወቅም፤ ትራምፕ ለሶስተኛ ጊዜ አሜሪካ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች እያሉ ይገኛሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከባድ ሙስና የተከሰሱትን 4 ተከሳሾችን፤ ፖሊስ ፍርድ ቤት ማቅረብ ሳይችል ቀረ

በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በፖሊስ የ'ይፈለጋሉ" ማስታወቂያ የወጣባቸው...

ስለመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ውጥረት እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች

🔸 ትላንት ምሽት ከኢራን ግዛት የተተኮሰ የሮኬት ጥቃት በሰሜናዊ...

የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉ በጋዜጣ እስኪታተም ረቂቅ ሰነዶችን ከመጠቀም እንዲቆጠብ የፍትሕ ሚኒስቴር አሳሰበ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ...

ፔንታጎን የእስራኤል ስለላ እንደሚያሳስበው ተገለጸ

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፔንታጎን እስራኤል ከፍተኛ ልዑኮችን ጨምሮ የአሜሪካ...