ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ወሽመጥን “አዲስ የአሜሪካ ግዛት” ማለታቸውን ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ካዚም ጋሪባባዲ “ቅዠታም” ሲሉ ፕሬዝዳንቱን ወርፈዋል።
“ዶናልድ ትራምፕ የፐርዥያ ባሕረ ሰላጤን በትክክል መጻፍ እንደተማሩት ሁሉ ስለ ሆርሙዝ ወሽመጥ ያላቸውን ቅዠትም በቅርቡ እናስተካክለዋለን” ሲሉ ጽፈዋል።
ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያቸው በለጠፉት ምሥል ላይ የሆርሙዝ ወሽመጥን አክብበው “የአሜሪካ አዲስ ግዛት” ሲሉ ጽፈዋል።
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርም ይሄንን ምሥል በድጋሚ አጋርተዋል።
በሌላ በኩል የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ መሐመድ ባጋር ጋሊባፍ በበኩላቸው አሜሪካ የመግባቢያ ሰነዱን ስምምነቶች ካልተገበረች የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደማይከፈት አስታውቀዋል።
BBC
