ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰን በላውራ አዋርድ እጩ ሆና ቀረበች

Date:


በየአመቱ ስኬታማ ጊዜን ያሳለፉ ስፖርተኞች እውቅና የሚያገኙበት የላውራ አዋርድ በፓሪስ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ያገኙ 6 አትሌቶች እጩ ሆነው ቀርበውበታል።

በሴቶች ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሀሰን ዕጩ ስትሆን አትሌቷ በፓሪስ ኦሎምፒክ በማራቶን የወርቅ በ5ሺ እና በ10ሺ ደግሞ የነሀስ ሜዳልያ ማሳካቷም ይታወሳል።

በፓሪስ 2024 በ1500 ሜትር የወርቅና በ5ሺ ሜትር የብር ሜዳልያ ያገኝችው ኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕየጎን አሜሪካዊቷ ማክ ላህሊን ሌቭሮን እና የሴንት ሉቺያዋ ጁሊያን አልፍሬዝ በሴቶች ዘርፍ በእጩነት የቀረቡ ሆነዋል።

በወንዶች ዘርፍ ደግሞ የምርኩዝ ዘላዩ ሙንዶ ዱፕላቲን እና የአጭር ርቀት ሯጩ የቦትስዋናው ሌትሲል ቴቦጎ ታጭተዋል።

በ7 ዘርፎች እውቅና በሚሰጥበት የላውራ ሽልማት ከአትሌቲክሱ ውጭ ሲሞን ባይልስ እና ካርሎስ አልካሬዝን ጨምሮ በርካቶች በእጩነት ተካተዋል።

ለ25ኛ ጊዜ በሚካሄደው ላውራ አዋርድ የመጨረሻው አሸናፊ ሚያዚያ 13 ቀን በማድሪድ የሚታወቅ ይሆናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ ከኢራን ጋር የተስማሙባቸውን ነጥቦች ከአርብ በፊት ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙባቸውን...

‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ የመጽሐፉ ዓይነት፡-...

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...