ናይጄሪያ የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫን አሸነፈች

Date:

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የሰነበተው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ሌሊት ሰባት ሰአት አካባቢ ተጠናቋል።

ለፍፃሜ የደረሱት ሞሮኮና ናይጄሪያ ያደረጉት ጨዋታ ማራኪ ፉክክርን አስተናግዷል።

ሞሮኮዎች በቺዝላን ቼባክና ፣ በሳና ምሶዴ ሁለት ግቦች 2 ለ 0 ሲመሩ ቆይተው በስተመጨረሻ 3 ለ 2 ተሸንፈዋል።

የናይጄሪያን ሶስት ግቦች ኤስቴር ኦኮሮንኮ ፣ ፎላሻድና ጄኒፈር ኢቼጊኒ አስቆጥረዋል።

ሞሮኮ ለሁለት ተከታታይ ግዜያት ለአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ደርሳ ስትሸነፍ  ናይጄሪያ ለ10ኛ ግዜ ዋንጫውን አንስታለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...