ከ50 በላይ አባላትን ያካተተ የሰላም ልዑክ መቐለ ገባ

Date:

ከኢትዮጵያ 12 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ50 በላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች እና ነጋዴዎችን ያካተተ የሰላም ልዑክ መቐለ ገባ።

ልዑካን ቡድኑ መቀለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በ ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአሁኑ ሰዓት ልዑኩ ከፕሬዝዳንት ታደሰ እና ከካቢኔ አባሎቻቸው ጋር መገናኘታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በተጨማሪም ልዑኩ ክፍፍሎችን ለማጥበብ እና ሰላምን ለማጠናከር ከፖለቲካ፣ ከሃይማኖት እና ከሲቪክ መሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሏል።

ይህ ጉዞ በዚህ ወር ወደ ትግራይ የተደረገው ሁለተኛው የሰላም ልዑክ ጥረት ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የተመራ ልዑክ ወደ መቀለ በማምራት ከትግራይ ክልል መሪዎች ጋር ተወያይቷል።

የሃይማኖት አባቶቹ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከፌደራል እና ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

ልዑኩ ወደ ትግራይ ያመራው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ “ትግራይ ወደ ግጭት፤ ወደ ጦርነት እንዳይገባ በሀገሪቱ የሚገኙ የሐይማኖት አባቶች በአቸኳይ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፤ ከተጀመረ በኋላ ብትናገሩ ዋጋ የለውም” ሱሊ ካስጠነቀቁ ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው።

ከዚህ ልዑክ ጉዞ በኋላ ከትግራይ የተውጣጡ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸውም ይታወሳል።

በውይይቱ በተለይም የተፈናቃዮች ጉዳይ፣ የትግራይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚዊ ሁኔታዎች ላይ በዋናነት ምክክር የተደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች እንደነበሩ ተገልጿል። የትግራይ ሃይማኖት አባቶችም ወደ መዲናዋ በመምጣት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸው መገለጹ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...