ናይጄሪያ የካካዋ ኢንዱስትሪን ከፍ በማድረግ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ያስችላል የተባለ አዲስ ተቆጣጣሪ ቦርድ ልታቋቁም ነው።
ከሠላሳ ዘጠኝ ዓመታት በኋላ መንግሥት አዲስ ተቆጣጣሪ አካል ለማቋቋም በዝግጅት ላይ ሲሆን የግብርና ሚኒስትር አቡበከር ኪያሪ የፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ ካቢኔ ኢንዱስትሪውን የመቆጣጠር ሃላፊነት ያለው ብሄራዊ የካካዋ አስተዳደር ቦርድ ለመፍጠር ረቂቅ ህግ ማፅደቁን አስታውቀዋል።
ናይጄሪያ ወደ ውጭ የምትልከው የካካዋ ዋጋ በ2023 እና 2024 መካከል ከሰባት እጥፍ በላይ ወደ 2.7 ትሪሊዮን ናይራ (1.7 ቢሊዮን ዶላር) ከፍ ብሏል፣ ይህም በከፍተኛ ፍላጎት እና በናይራ ዋጋ መቀነስ ምክንያት እንደሆነ የአፍሪካ ቢዝነስ ዘገባ ያሳያል ።
