አሜሪካን በኢራንና እስራኤል ጦርነት ጣልቃ እንዳትገባ ሩሲያ አስጠነቀቀች

Date:

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋሽንግተን በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዳትወስድ አስጠንቅቋል።

እንደ ፋራንስ 24 ዘገባ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፤ “ዋሽንግተን በሁኔታው ላይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንዳትፈጽም ልናስጠነቅቅ እንወዳለን” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

“ማንኛውም የአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ሊተነበዩ የማይችሉ አሉታዊ መዘዞችን የሚያስከትል እጅግ አደገኛ እርምጃ ነው'” ሲሉም አክለዋል።

የሩሲያና የቻይና መሪዎች በስልክ ካደረጉት ውይይት በኋላ፤ የክሬምሊን አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሞስኮ እና ቤጂንግ የግጭቱ ፍጻሜ በፖለቲካዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ብቻ መፈታት አለበት ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከእስራኤል እና ከኢራን መሪዎች ጋር በስልክ ተነጋግረው ነበር።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...