የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተቋሙ አስታውቋል።
ተርነር እ.ኤ.አ በ1980 የመጀመሪያውን የ24 ሰዓት የኬብል የዜና አውታር በመክፈት በሚዲያው ዘርፍ አብዮት የፈጠሩ ሰው ነበሩ። በተለይም በገልፍ ጦርነት ወቅት በሰሩት የቀጥታ ስርጭት ዘገባ ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፉ ሲሆን፣ የእሳቸው ስኬት እንደ ፎክስ ኒውስ ላሉ ሌሎች ታላላቅ ጣቢያዎች መፈጠር ፈር ቀዳጅ ሆኗል።
የሲኤንኤን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ቶምፕሰን ተርነርን “ቁርጠኛና ፍርሃት የማያውቁ መሪ” ሲሉ የገለጿቸው ሲሆን፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፣ ተርነር በታሪክ ውስጥ ትልቅ አሻራ ካሳረፉ ታላላቅ ሰዎች አንዱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ተርነር በሚዲያው ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በስፖርትና በበጎ አድራጎት ስራዎቻቸውም የሚታወቁ አንጋፋ ስብዕና ነበሩ።
በተለይም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ1 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ በማድረግ የሚታወሱት ቴድ ተርነር፣ በ938 በኦሃዮ ተወልደው የአምስት ልጆች አባት ለመሆን በቅተዋል።
እኒህ ታላቅ ሰው በሚዲያው ዓለም ላይ ጥለውት ያለፉት አሻራ ለትውልድ ሲዘከር የሚኖር የታሪክ አካል ሆኖ ይቀጥላል።
