አሜሪካ እንዳይገባ የተከለከለው ሶማሊያዊ አሠልጣኝ ኦማር አርታን ሙሉ ክፍያ እንደሚሰጠው ፊፋ ገለጸ።የዓለም ዋንጫን ይዳኛል ተብሎ የነበረው አሠልጣኝ ግጥሚያዎችን መዳኘት ባይችልም እንኳን ሙሉ ክፍያው እንደሚሰጠው ፊፋ አስታውቋል።
ኦማር አርታን በማያሚ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለ11 ሰዓት መጠይቅ ከተደረገለት በኋላ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ተከልክሏል።የዲፕሎማት ፓስፖርቱ እና አንድ ጊዜ አሜሪካ እንዲገባ የሚፈቅደው ቪዛው ተቀባይነት አላገኙም።
የአሜሪካ ባለሥልጣን እንዳሉት አሠልጣኙ “በሽብርተኛነት ከተጠረጠሩ ቡድኖች ጋር ትስስር እንዳለው ስለሚታመን” ክልከላ ተጥሎበታል።
አሠልጣኙ ከአሜሪካ የኢምግሬሽን ባለሥልጣኖች ከአል-ሻባብ ጋር ግንኙነት እንዳለው ተጠይቆ ምንም ትስስር እንደሌለው መግለጹን ተናግሯል።“ሕጋዊ ሰነዶች ይዤ ነበር። ትክክለኛ ቪዛ ነበረኝ። ሕልሜን ለመኖር የምሞክር አሠልጣኝ ነኝ።
ትልቁ ሕልሜ የዓለም ዋንጫን መዳኘት ነበር” ብሏል።ወደ ቱርክ የሚጓዝ አውሮፕላን ውስጥ እንዲገባ ከተደረገ በኋላ ወደ ሶማሊያ እንዲመለስ ፊፋ እገዛ ማድረጉ ተገልጿል።ሞቃዲሹ ሲገባም ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
