አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በተጠናቀቀው ሂሳብ ዓመት የ1.8 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ

Date:

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ፈታኝ በሆነው የኢኮኖሚ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም የላቀ የፋይናንስና የአሠራር ውጤት በማስመዝገብ፣ ከግብር በፊት 1.8 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

ይህ ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ94% ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ ባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘቡ በ23% በማደግ 44.0 ቢሊዮን ብር እንደደረሰና ጠቅላላ ብድርና ቅድሚያ ክፍያው ደግሞ በ19% ጨምሮ 36.2 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል።

የባለአክሲዮኖችን 21ኛዉ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ያደረገው አንበሳ ባንክ፣ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማሻሻል የቅርንጫፍ መረቡን በ35 አዳዲስ መውጫዎች በማስፋፋት ጠቅላላ 341 ቅርንጫፎች ያደረሰ ሲሆን፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑ ላይም ሰፊ ዕድገት አስመዝግቧል።

በዚህ አፈጻጸም የተነሳ፣ የባንኩ ጠቅላላ ንብረቶች በ25% አድገው 54 ቢሊዮን ብር ሲደርሱ፣ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ በ21% በማደግ 3.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን በዓመታዊ ሪፖርቱ አስታዉቋል።

Via Capital

@Addis_News
@Addis_News

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...